የግብፅ ፕሬዚዳንት አብዱልፈታህ አልሲሲ እስራኤልን በጠላትነት ፈረጁ።
አልሲሲ “እመኑኝ እስራኤል ጠላታችን ናት” ሲሉ ተደምጠዋል።
ፕሬዚዳንቱ አክለውም፣ “ጠላት በእኛ ላይ ያለውን አመለካከት መቀየር አስፈላጊ ነው” ብለዋል።
“እስከዛሬ ይህን ቃል የሚጠቀሙት ፍልስጤማውያን ነበሩ” ያሉት አብዱልፈታህ አልሲሲ፣ “አሁን ግን ሁላችንም ተመሳሳይ አቋም የምናሳይበት ጊዜ ላይ እንገኛለን” በማለት ተናግረዋል።
ግብፅ እስራኤልን በጠላትነት ስትፈርጅ ከ1977 ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑ ተገልጿል።
የፕሬዚዳንት አልሲሲ ንግግር ግብፅ በእስራኤል በኩል የደህንነት ስጋት ውስጥ መግባቷን ያመላከተ ተደርጎ ተወስዷል።
