በኢንስትራክተር መሰረት የማኔ የሚመራዉ የመቻል ሴቶች ቡድን በዝዉዉሩ የነቃ ተሳትፎን በማድረግ የወቅቱ የሴቶች ፕሪሚርሊግ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ የሆነችዉን ሴናፍ ዋቁማን ከኢትዮጲያ ንግድ ባንክ ማስፈረም ችሏል።
ሴናፍ በመቻል ቤት የአንድ አመት ዉል የሚኖራት ሲሆን ወደ ዲሲ ዩናይትድ ክለብ ለመግባት የምታደርገዉ ሙከራ የሚሳካ ከሆነ በመኋል ከመቻል ጋር ልትለያይ እንደምትችል ታዉቋል።
ግብ አዳኟ አጥቂ መነሻዋን በጥሩነሽ ዲባባ ስፖርት አካዳሚ በማድረግ በሊጉ በአዳማ ከተማ እና በነገሰችበት ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ የሁለት አመት ቆይታ ሲኖራት በተከታታይ አመት በሴቶች ፕሪሚርሊግ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ሁና መጨረሷም አይዘነጋም ።
