ሩሲያ እና ዩክሬን በኢስታንቡል ለድርድር መቀመጣቸው ለዓለም ሰላም መልካም ተስፋ ነው

Date:

ድርድሩ ጥሩ የሰላም ጅምር ነው ሲሉ በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ኢኒስቲትዩት የጥናትና ምርምር መሪ የሆኑት ዳርእስከዳር ታዬ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። አክለውም ዘላቂ ሰላም የግጭቱን ዋና መንስዔዎች መፍታት እንደሚሻ ጠቁመዋል።

🗣 “ለሩሲያውያን የግጭቱ ዋና መንስዔ የኔቶ ወደ ምስራቅ አውሮፓ መስፋፋት ነው። ሌላው ደግሞ ዩክሬን ሩሲያኛ ተናጋሪዎች ላይ የምታደርሰው በደል ነው” ብለዋል።

ተመራማሪው አውሮፓውያን ግጭቱ እየሄደ ባለበት መንገድ ደስተኛ እንዳልሆኑ፣ ዩክሬን እንድታሸንፍ እና ሩሲያን ድል ማድረግ እንደሚፈልጉ ገልፀው፤ ይህ የማይሆን ነው ብለዋል።

በአውሮፓውያን እና በአሜሪካውያን መካከል የተፈጠረው ወቅታዊ ልዩነት አሜሪካ ሰላምን እንድትመርጥ፤ አውሮፓ ግን ግጭቱ ይቀጥል የሚል አቋም እንድትይዝ ያደረገ ይመስላልም ብለዋል።

ይህ ክፍፍል መቀጠሉ ላይ ጥሪጣሪያቸውን የገለፁት ተመራማሪው፤ አውሮፓውያን ተቀበሉትም አልተቀበሉትም ሩሲያ እና ዩክሬን ስምምነት ላይ ይደርሳሉ ብለው ተስፋ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...