በመቶዎች የሚቆጠሩ የደቡብ ትግራይ መኾኒ ከተማ ነዋሪዎች፣ ዛሬ በሕወሓት ላይ የተቃውሞ ሰልፍ ማድረጋቸውን የክልሉ የዜና ምንጮች ዘግበዋል።
ነዋሪዎቹ ሰልፍ የወጡት፣ ሕወሓት የደቡብ ትግራይ አስተዳደራዊ መዋቅሮችን አፍርሶ በድጋሚ ለማደራጀት ማቀዱን የሕወሓት ሊቀመንበር ደብረጺዮን ገብረሚካኤል በቅርቡ ለወይን መጽሄት በሠጡት ቃለ ምልልስ መናገራቸውን በመቃወም ነው።
በተቃውሞ ሰልፉ ላይ”የራያ ህዝብ ድምፅ ይከበር፣ የደብረፂዮንን መግለጫ አጥብቀን እንቃወማለን፣ በመስዋዕትነት ስም ህዝብ መማገድ ይቁም” የሚሉ መፈክሮች ተስተጋብተዋል፡፡
ከትናንት ወዲያ በደቡብ ትግራይ የማይጨው ከተማ ነዋሪዎች፣ ተመሳሳይ የተቃውሞ ሰልፍ ማድረጋቸው ይታወሳል።
(ዋዜማ)
