“ኢቴክስ 2025 ” የተሰኘ የቴክኖሎጂ ኤክስፖ በኢትዮጵያ ኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር እና በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢኒስቲትዩት አዘጋጅነት በዛሬው እለት ተከፍቷል ።
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ትግስት ሃሚድ ፤ፈጠራን እና የድጅታል እድገትን የሚያፋጥነውን ኢቴክስ 2025 በማዘጋጀታችን ደስተኞች ነን ብለዋል።
ዋና ዳይሬክተሯ ይህ ኩነት የኢትዮጵያን የድጅታል ራዕይ በማሳደግ በኩል ከፍተኛ አስተዋፅኦ አለው ብለዋል።
ኤክስፖው የኢትዮጵያን የቴክኖሎጂ አቅምን ለማስተዋወቅ እና ለማሳደግ እንዲሁም በዚህ ዘርፍ ላይ ከተሰማሩ አለም አቀፍ ሀገራት ጋር ትስስር ለመፍጠር ያግዛልም ብለዋል።
ኤክስፖ አለም የሳይበር ወንጀልን ለመከላከል እያደረገ ባለው ጥረት ላይ ኢትዮጵያ ቁልፍ ተዋናይ እንድትሆን እንዲሁም በቴክኖሎጂው ዘርፍ የተሰሩና እየተሰሩ ያሉ ጥረቶችን ለአለም ለማሳየት ይረዳል ተብሏል።
የቴክኖሎጂ ኤክስፖው ከ10 ሺህ በላይ ሰዎች የሚሳተፉበት ሲሆን ተሳታፊዎቹ ከተለያዩ 45 ዓለም ሀገራት የተውጣጡ መሆናቸው ተሰምቷል።
እንደ ሜታ፣ ሁአዌና ኖኪያ የመሳሰሉ ግዙፍ ዓለምአቀፍ የቴክኖሎጂ ኩባንያችና መሪዎች የዚህ ኤክስፖ አካል ናቸው።
በዛሬው እለት በተከፈተው ኢቴክስ 2025 ላይ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አፅቀ ስላሴን ጨምሮ የፖሊሲ አውጪዎች፣በዘርፉ ላይ ያሉ ሙሁራን፣ጀማሪ ስራ ፈጣሪዎች፣ኢንቬስተሮች ተገኝተዋል።
