በባንኮች መካከል የውጭ ምንዛሬ መገበያየት የሚያስችል የግብይት አውታር ተጀመረ

Date:

በሀገሪቱ የፋይናንስ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ አውቶሜትድ ሥርዓት የሚካሄደው ግብይቱ በኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ መድረክ ላይ ሁሉም ንግድ ባንኮች ስለ ገበያው እኩል መረጃ ኖሯቸው የሚከናወን መሆኑን ብሔራዊ ባንክ በይፋዊ መግለጫው አስታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ዶ/ር ኢዮብ ተካልኝ፣ “ለተሳታፊ ሁሉ ግልጽ፣ ፈጣንና በመመሪያ የተመራ የገበያ አካባቢ ይፈጥራል። መድረኩ የገበያ ዲሲፕሊንን ለማጠንከር፣ የዋጋ ሂደትን ለማሻሻልና የፋይናንስ ገበያ ሪፎርምን ለመደገፍ ትልቅ ግብዓት ነው።” ሲሉ በማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ ተናግረዋል፡፡

የገበያው አሠራር በብሔራዊ ባንክ መመሪያዎች የሚመራ ሲሆን፣ ሁሉም ተሳታፊ ባንኮች የተቀመጡ የሥነ-ምግባር ደንቦችን እና የውጭ ምንዛሬ ተጋላጭነት ገደቦችን የማክበር ግዴታ እንዳለባቸው ተጠቁሟል።

ይህ እርምጃ የኢትዮጵያን የፋይናንስ ገበያ ከዓለም አቀፍ አሠራሮች ጋር ለማጣጣም እና የውጭ ምንዛሬ አስተዳደርን ይበልጥ ዘመናዊ ለማድረግ ያለመ መሆኑም ተመላክቷል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...