የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች ከአሜሪካ ኤምባሲ ጋር ተወያዩ

Date:

የ”ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት” አመራሮች በዛሬው ዕለት ከአሜሪካ ኤምባሲ አመራሮች ጋር ውይይት ማድረጋቸውን አሕአፓ አስታውቋል፡፡

ፓርቲው በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባጋራው መረጃ፤ በውይይቱ ላይ ወቅታዊ ሁኔታዎች፣ የፖለቲካ እስረኞች፣ የሚዲያ አፈና፣ የጦርነት ጉዳይ፣ የንጹሀን እልቂትን እንዲሁም አጠቃላይ የፖለቲካ ምሕዳሩን ወደ መከርቸም መሄድ የተመለከቱ ሀሳቦች መነሳታቸውን ጠቁሟል፡፡

የቅንጅቱ አመራሮች፤ ቅንጅቱ በትግል ላይ ያሉ ሁሉም አካላት የሚያምኑበት ትክክለኛ ፖለቲካዊ ድርድር ተደርጎ ጦርነቶች እንዲቆሙ፣ የንጹሀን ግድያ እንዲበቃ፣ ሁሉም የፖለቲካና የማንነት እስረኞች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ፣ እንዲሁም የፖለቲካ ምሕዳሩ እንዲሰፋ ትግሉን እንደሚቀጥልና በተጠቀሱት ጉዳዮች ላይ ጠንካራ አቋም እንዳለው ለስራ ሀላፊዎቹ መግለጹን ፓርቲው አመልክቷል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...