በኢራን የአገዛዝ ለዉጥ ለማድረግ አስበናል

Date:



‎የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በመካከለኛው ምስራቅ በቅርብ ጊዜ ውስጥ “በሚገርም ሁኔታ”የአገዛዝና የስርአት ለዉጦች እንደሚኖሩ መናገራቸው ተሰማ ።

‎ ኔታንያሁ ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ባደረጉት ንግግር በኢራን ውስጥ ስላለው የስርዓት ለውጥ ፍንጭ ሰጥተዋል። ተብሏል

‎በትዕግስት የቆዩት የኢራን ሰዎች ነፃነታቸውን መልሰው ያገኛሉ። ኢራንን እንደገና ታላቅ ያደርጉታል። ብለዋል ።

‎ከቅርብ አመታት ወዲህ ኢራን በአያቶላህ ላይ በርካታ ህዝባዊ አመፆች ስታስተናግድ ቆይታለች፤ ይህ ደግሞ ስለ ኢስላሚክ ሪፐብሊክ የወደፊት እጣ ፈንታ ጥያቄ አስነስቷል ያሉት ፕሬዘዳንቱ “ በእስራኤል ላይ ጦርነት የከፈቱት ጠፍተዋል ለወደፊቱም እስራኤልን በክፉ የሚያዩ ይጠፋሉ” ብሏል።

‎ “ደፋር ሰላም ፈጣሪዎች ቦታቸውን ይወስዳሉ
‎የእስራኤል እና የኢራን ሰዎች ወዳጅነታቸውን ያድሳሉ እናም ሁለቱ ፣ ሁለቱ ጥንታውያን ህዝቦቻችን፣ የእስራኤል ህዝቦች እና የኢራን ህዝቦች መላውን ዓለም የሚጠቅም ወዳጅነት ይመልሳል” ሲሉም አክለዋል።

‎እ.ኤ.አ. በ 1979 ከኢራን አብዮት በፊት እስራኤል እና ኢራን የረዥም ጊዜ ግንኙነት ነበራቸው ፣የምዕራባውያን ወዳጃዊ ሻህ በአያቶላዎች ከተገረሰሰ በኋላ ጀምሮ ኢራን በአካባቢው ትልቁ የእስራኤል ጠላት ሆናለች እና ተላላኪዎቿን ማለትም ሃማስን፣ ሂዝቦላህን፣ ሁቲዎችን እና ሌሎች በመካከለኛው ምስራቅ የሚገኙ የሺዓ ሚሊሻዎችን በመጠቀም በእስራኤል መንግስት ላይ ጦርነት ስታደርግ ቆይታለች።

‎እስራኤል በበኩሏ በስዉርና በይፋ የኢራንን ቁልፍ መሪዎችና የኢራንን አጋሮች ስታጠቃ መቅየቷ ይታወሳል ሲል ኢንደመያ አክስፕረስ አስነብቧል ።

‎‎የኔታ ቲዩብ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...