ዘመናዊ መኪና የሚያሸልመው ፤ በሺዎች የሚቆጠሩ የዲያስፖራው ማህበረሰብ አባላት በየዓመቱ የሚሳተፉበት የግራንድ አፍሪካን ረን የ5ኪሜ የመዝናኛ ሩጫ ዝግጅት በመጪው ኦክቶበር በዋሽንግተን ዲሲ ከተማ ለ8ኛ ዓመት ሊካሄድ መሆኑ ተገለፀ።
እ.አ.አ በኦክቶበር 10 2026 በሚካሄደው ዝግጅት ከሚካፈሉ ተሳታፊዎች መካከል እድለኛ የሆነ ባለዕጣ የ2026 ቶዮታ ኮሮላ መኪና በዝግጅቱ ማጠናቀቂያ ላይ የዕጣ ማውጣት ስነስርዓት ተከናውኖ እንደሚሸለም ታውቋል።
የመኪና ሽልማቱ የዝግጅቱ ቀዳሚ አጋር በሆነው አሌክሳንድሪያ ቶዮታ የተዘጋጅቶ የሚቀርብ እንደሆነ ተገልፆል። እንደሁልጊዜውም በዚህ ዝግጅት ላይ ታላላቅ አትሌቶች እና የኪነጥበብ ባለሞያዎች በክብር እንግድነት እንደሚሳተፉም አዘጋጁ ኖቫ ኮኔክሽንስ የላከው ጋዜጣዊ መግለጫ ይጠቁማል።
“ቅድሚያ ለማህበረሰብ” በሚል መረሃ-ግበር የዝግጅቱ አጋር ሆኖ ለአለፉት 5 ዓመታት የቆየው እና ለቀጣዮቹ ዓመታት በአጋርነት የሚቆየዉ የአሌክሳንደሪያ ቶዮታ የጄነራል ማኔጀር የሆኑት አቶ ያሬድ ማን አለብህ እንደገለፁት፣ ግራንድ አፍሪካ ረን ከሩጫም በላይ ለዳያስፖራው ማህበረሱብ የመገናኛ እና ለበጎ አድራጎት ድርጅቶች የገንዘብ ማሰባሰቢያ መድረክ ሆኖ የሚያገለግል ከመሆኑም ባሻገር የድርጅታቸው የረጅም ጊዜ ደንበኞቹን ለማመስገን በዝግጅቱ ላይ ሽልማት እንደሚያቀርቡ ገልፀዉ፣ የአሌክሳንደሪያ ቶዮታ ከዳያስፖራው ማህበረስብ ጎን በቀጣይነትምበኣጋርነት እንደሚቆም ጠቁመዋል።
የመዝናኛ ሩጫው ዋና አዘጋጅ የሆኑት ዶክተር ጋሻው አብዛ ዝግጅቱ ከአንድ ቀን የ5 ኪሜ የቤተሰብ ሩጫነት የበለጠ ፋይዳ ያለው መርሀግብር መሆኑን ጠቁመው፤ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያንን ብሎም አፍሪካዊያንን በማቀራርብ ረገድ ጉልህ ሚና እንዳለው ገልፀዋል።
የመኪና ስጦታዉ ለአንድ ዕድለኛ ከሚያበረክተው እገዝ ጎን ለጎን የዕጣ ማውጣቱ ሂደት በዝግጅቱ ቀን አዝናኝ እና አጓጊ ሆኖ እንዲከናውን እየተሰራበት መሆኑንም አዘጋጆቹ ገልፀዋል፡፡
የዘንድሮው ለ4ኛ ጊዜ በስጦታነት የሚቀረብ የቶዮታ መኪና ነው። የግራንድ አፍሪካ ረን ምዝገባ በዝግጅቱ ድረ-ገፅ www.africanrun.com ላይ ከሰኔ ወር መጀመሪያ አንስቶ እንደሚጀመር አዘጋጆቹ አያይዘው አንስተዋል።
በዘንድሮው የ‘ግራንድ አፍሪካን ረን’ ለዕድለኛ ተሳታፊ ዘመናዊ የቶዮታ መኪና በዕጣ እንደሚቀርብ ተገለፀ
Date:
