“የኒውክሌር ባለሙያዎች ከሌሉ ስምምነቱ አደገኛ ነው”

Date:



የአውሮፓ ኅብረት የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ኃላፊ ካጃ ካላስ፣ በኢራን የኒውክሌር ድርድር ዙሪያ የዘርፉ ባለሙያዎች ካልተሳተፉ የሚደረገው ስምምነት “ደካማ” እና ለዓለም ሰላም አስጊ ሊሆን እንደሚችል አስጠነቀቁ።

በቆጵሮስ በተካሄደው የአውሮፓ ኅብረት መሪዎች ጉባዔ ላይ እንደተገለጸው፣ የኒውክሌር ባለሙያዎች የሌሉበት ውይይት ኢራን ከዚህ ቀደም የነበሩትን ገደቦች እንድትጥስና ይበልጥ አደገኛ እንድትሆን ዕድል ሊሰጣት ይችላል።

በተለይም እ.ኤ.አ በ2015 የተደረገው ስምምነት ፈርሶ በነበረበት ሁኔታ፣ አዲሱ ድርድር ጥንቃቄ ካልተደረገበት ከበፊቱ የከፋ የደህንነት ስጋት ሊደቅን እንደሚችል ካላስ ስጋታቸውን ገልጸዋል።

ኃላፊዋ አክለውም፣ የኢራን የኒውክሌር ጉዳይ ብቻ ሳይሆን የሚሳዔል ፕሮግራሞቿ፣ ለታጣቂ ቡድኖች የምታደርገው ድጋፍና በአውሮፓ ውስጥ የምታካሂዳቸው የበይነ-መረብ (Cyber) ጥቃቶች አብረው መፈታት እንዳለባቸው አሳስበዋል።

እነዚህ ዘርፈ-ብዙ ችግሮች እልባት ካላገኙ፣ ኢራን በክልሉና በዓለም አቀፍ ደረጃ ያላት አስጊነት ይበልጥ አደገኛ እየሆነ እንደሚሄድ ተመልክቷል።

ማንኛውም ስምምነት የሀገሪቱን የኒውክሌር እንቅስቃሴ በትክክል መገደብና ዓለም አቀፍ ተቆጣጣሪዎች ወደ ቴህራን እንዲገቡ የሚያስችል ጠንካራ ማዕቀፍ ሊኖረው እንደሚገባም ተገልጿል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...