ባንኮች ከጡረታ መዋጮ የአገልግሎት ክፍያ በሚል መቁረጥ አይችሉም ተባለ

Date:



አንዳንድ ባንኮች የጡረታ ክፍያ ለተጠቃሚዎች ሲክፍሉ የአገልግሎት ክፍያ በሚል እንደሚቆርጡ ተነግሯል።

የአገልግሎት ክፍያውን እየቆረጡ ያሉት ብሄራዊ ባንክ መመሪያ አውጥቷል በሚል እንደሆነ ተጠቅሷል።

በ2014 የወጣው የጡረታ አዋጅ ግን ከጡረታ መዋጮ ገንዘብ ላይ ቀንሶ ለአገልግሎት ክፍያ፣ ለገንዘብ ማስተላለፊያ እያሉ መጠቀም እንደማይቻል ይደነግጋል ተብሏል።

ብሄራዊ ባንክ አወጣው የተባለው  መመሪያ ከአዋጁ በላይ ሊሆን ስለማይችል ግን ተግባሩ ሊቆም ይገባል ሲሉ የአስተዳደሩ የህግ ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ግርማ ሢሣይ አሳስበዋል።

የግል ድርጅት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር በጡረታ አዋጁ ዙሪያ ከሚመለከታቸው ጋር በኢሊሊ ሆቴል እያካሄደ ነው።
ሸገር 102.1

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለ10 ምሁራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጥቷል

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ቦርድ ጥቅምት 12 ቀን 2019...

ዳሸን ባንክ እና ሼባ ማይልስ የፕላቲንየም ብራንድ የማስተር ካርድ ይፋ አደረጉ

ዳሸን ባንክ እና ሼባ ማይልስ በኢትዮጵያ ለሚገኙ ደንበኞች የፕሪሚየም...

የአሜሪካ የደህንነት ኃላፊ ኢራንን አስጠነቀቁ

ቡሔራዊ ደህንነት ዳይሬክተር ጄይ ክላይተን አርብ ዕለት ኢራን በውጭ...

ኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ  በአመት ከ1.1 ቢሊዮን ዶላር በላይ ታጣለች

85 በመቶ የሚሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ በግብርናው ዘርፍ የተሰማራ ሲሆን...