ቤልጅየም በትምህርት ቤቶች ውስጥ የሞባይል ስልኮችን መጠቀምን በሕግ ከለከለች

Date:

ቤልጅየም እ.ኤ.አ ከ2025/2026 የትምህርት ዘመን ጀምሮ በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሞባይል ስልኮችን እና ሌሎች የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎችን መጠቀም እንደማይቻል አስታውቃለች።

የጤና እክል ወይም ድንገተኛ አደጋዎች ካልተፈጠሩ በስተቀር የሞባይል ስልኮች በሀገር አቀፍ ደረጃ እንደሚታገዱ የቤልጅየም የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

እገዳው በሁሉም ክልሎች ተግባራዊ ይሆናል የተባለ ሲሆን፤ ስልክ ይዘው በተገኙ ላይ ትምህርት ቤቶች ራሳቸው የዲሲፕሊን ርምጃዎችን እንደሚወስኑ ተገልጿል።

በብራስልስም በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሞባይል ስልኮችን መጠቀም ካለፈው የትምህርት ዘመን ጀምሮ ሙሉ በሙሉ የተከለከለ ሲሆን፤ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ደግሞ አጠቃቀምን ለመከላከል ጥብቅ ገደቦችን አውጥተዋል ሲል አናዶሉ ዘግቧል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...