ትራምፕ ለኖቤል የሰላም ሽልማት ታጩ  

Date:


የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ በዋይት ሀውስ ተገናኝተዋል ።ሁለቱ መሪዎች በእስራኤልና ሀማስ መካከል እየተካሄደ ያለውን ጦርነት ለማስቆም እና የተኩስ ስምምነት ላይ መድረስ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መምከራቸው ከዋይት ሀውስ የወጡ መረጃዎች ጠቁመዋል ።ይህ በእንዲህ እንዳለ የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ በዋይት ሀውስ ባደረጉት ንግግር  ዶናልድ ትራምፕ  ለኖቤል የሰላም ሽልማት  እጩ አድርገው ማቅረባቸውን ገልጸዋል ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለኖቤል የሰላም ሽልማት ኮሚቴ የአሜሪካውን ፕሬዝዳንት እጩ በማድረግ የላኩትን ደብዳቤ ለትራምፕ አቅርበዋል።

ኔታንያሁ ትራምፕ “በብዙ አገሮች በተለይም በመካከለኛው ምስራቅ ሰላምና ፀጥታ እንዲሰፍን እየሰሩ ነው” በማለት ትራምፕን አሞካሽተዋል። ሽልማቱ ይገባዎታል፣ እናም ሊያገኙት ይገባል” ሲሉም ነው  ኔታንያሁ የተናገሩት ።

ትራምፕ በበኩላቸው ይህ ከኔታንያሁ መምጣቱ “ትልቅ ትርጉም አለው” ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል ።

ለኖቤል የሰላም ሽልማት እጩነት ማቅረብ ክፍት ሂደት ሲሆን ትራምፕ በዚህ አመት ለሽልማቱ ታጭተዋል።

ዘገባው የ ዘ ታይም ኦፍ እስራኤል እና አልጄዚራ ነው

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...