ቻይና ለ 74 ሀገራት ከቪዛ ነፃ ጉዞን ፈቀደች

Date:

በዚህ ዝርዝር ዉስጥ አንድም የአፍሪካ አገር አልተካተተም፡፡

ከሐምሌ 16 ጀምሮ ተግባራዊ በሚደረገው በዚ የነፃ ቪዛ ጉዞ የተፈቀደላቸው 74 ሀገራት፤ ለ 30 ቀናት ወደ ቻይና ያለ ቪዛ መጓዝ እንደሚችሉ ተነግሯል።

የሀገሪቷን የቱሪዝም ገቢ ለማሳደግ ትግበራ ላይ ይውላል የተባለው ከቪዛ ነፃ ጉዞ፤ የአፍሪካ ሀገሮችን ግን ሳያካትት ቀርቷል ።

ይህ የነጻ ቪዛ ጉዞ በኮቪድ ምክንያት የተጎዳውን የሀገሪቷን የቱሪዝም ኢንዱስትሪ በከፍተኛ ደረጃ እንዲያንሰራራ ይረዳል ተብሏል።

ሆኖም ቻይና ይህን ዕድል ለሌሎች አገራት ስትፈቅድ አንድም የአፍሪካ አገር ያለማካተቷ በአፍሪካ ያላትን ተሳትፎ ለማሳደግ በቅርብ ጊዜያት ካደረገችው ጥረት ጋር የሚቃረን ነው ሲል አፍሪካ ኒውስ ዘግቧል።

ሐምሌ 2 ቀን 2017 ዓ.ም

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...