አቢሲንያ ባንክ በኢንስትራክተር መንግስቱ ወርቁ ስም ቅርንጫፍ ከፈተ

Date:

አቢሲንያ ባንክ በቀድሞው የኢትዮጵያ እግርኳስ ብሔራዊ ቡድን ተጨዋች እና አሰልጣኝ ኢንስትራክተር መንግስቱ ወርቁ ስም አዲስ አበባ ሰሚት ኮንዶሚኒየም አካባቢ አዲስ ቅርንጫፍ ከፍቷል።

በኢንስትራክተሩ ስም ቅርንጫፍ  መከፈቱ  ለኢትዮጵያ አስተዋጽኦ ያደረጉ ባለውለታዎች እንዲታወሱና እንዲዘከሩ የሚያደርግ መሆኑም በቅርንጫፉ  የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት ላይ ተገልጿል።

በሥነ ሥርዓቱ ላይ የተገኙት  የኢትዮጵያ እግር ኳስ ብሔራዊ ቡድን የቀድሞ አሰልጣኝ  ኢንስትራክተር ሰዉነት ቢሻዉ፤ የሀገር ባለዉለታ የሆኑ ሰዎች እንዲዘከሩ የሚያደርጉ መሰል እንቅስቃሴዎች ሙያና ሙያተኛን የሚያስከብሩ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ኢንስትራክተር መንግስቱ ወርቁ ለቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ቡድንና ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በርካታ ጨዋታዎችን ያደረጉ እውቅ እግር ኳስ ተጨዋች የነበሩ ሲሆን፣ ለብሔራዊ ቡድን ከ60 በላይ ጎሎችን አስቆጥረዋል። የኢትዮጵያ ክለቦችንና ብሔራዊ ቡድንን በማሰልጠንም ውጤታማ ሥራ ስለመሥራታቸው የሕይወት ታሪካቸው ያስረዳል።

በመክፈቻ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የባንኩ ከፍተኛ ኃላፊዎች እና  የቀድሞ  እግርኳስ ተጨዋቾች ተገኝተዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...