አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ ተቀማጭ ገንዘቡን 44 ቢሊዮን ብር አደረሰ

Date:

ባንኩ ዛሬ ጥቅምት 22-2018 ዓ.ም 21ኛ መደበኛ የባለአክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባኤውን ባካሄደበት ወቅት አጠቃላይ የተቀማጭ ገንዘብ መጠኑን 44 ቢሊዮን ብር ማድረሱን አስታውቋል።

ባንኩ በዓመቱ መጨረሻ የደረሰበት የተቀማጭ ገንዘብ መጠን ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የብር 8.3 ቢሊዮን (23 በመቶ) ዕድገት አሳይቷል።

በበጀት ዓመቱም ከታክስ በፊት 1.8 ቢሊየን ብር በማትረፍ ካለፈው ዓመት አንፃር የ94 በመቶ ብልጫ ማስመዝገቡን የባንኩ ፕሬዝዳንት ዳንኤል ተከስተ ተናግረዋል።

ከዚህ ጋር ተያይዞ የደንበኞች ቁጥር ካለፈው በጀት ዓመት በ24 በመቶ ሲያድግ፤አጠቃላይ የደንበኞች ብዛት 2.4 ሚሊዮን መድረሱንም አንስተዋል።

እንዲሁም አንበሳ ባንክ የአገልግሎት ተደራሽነቱን ለማስፋፋት በበጀት ዓመቱ አዋጭ በሆኑ በተለያዩ የአገሪቱ ከተሞች ተጨማሪ 35 አዳዲስ ቅርንጫፎችን በመክፈት  ጠቅላላ የቅርንጫፎቹን ቁጥር 3መቶ41 ማድረስ ተችሏል ብለዋል።

እስከ በጀት ዓመቱ መገባደጃም ጠቅላላ የሰራተኞቹን ብዛት 6 ሺህ8መቶ88 ማድረሱን የባንኩ ፕሬዝዳንት ጠቅሰዋል።

ጥቅምት 22/2018 ዓ.ም

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...