የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከኬንያው የኤሌክትሪክ ኃይል ኩባንያ (KPLC) ጋር አዲስ የኃይል ሽያጭ ስምምነት ተፈራረመ።
በስምምነቱ መሠረት ኬንያ በአንድ ኪሎ ዋት ሰዓት ኢነርጂ 24 ብር ከ07 ሳንቲም፣ እንዲሁም ለዲማንድ ቻርጅ 1,010 ብር ከ89 ሳንቲም ትከፍላለች።
አገልግሎቱ በላከልን መረጃ ስምምነቱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር ጌቱ ገረመው እና የKPLC ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር ኢ/ር ጆሴፍ ሲሮር በጋራ ፈርመውታል።
በድንበር አካባቢዎች አስተማማኝ የኃይል አቅርቦትን ለማስፋፋት፣ የሁለቱን ሀገራት የኢኮኖሚና ሰላም ትብብር ለማጠናከር እንዲሁም የምስራቅ አፍሪካን የተቀናጀ የኃይል አቅርቦት ሥርዓት (Regional Power Pool) እውን ለማድረግ ያለመ ነው።
