ከሐይማኖታዊ መርህ ውጪ ጥላቻን የሚሰብኩ አካላት ሊታረሙ ይገባል

Date:


ኃይማኖትን ሽፋን በማድረግ ከሐይማኖታዊ መርህ ውጪ ጥላቻን የሚሰብኩ አካላት ከስህተታቸው ሊታረሙ ይገባል ሲሉ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ ተናገሩ።

የኢትዮጵያ ኃይማኖት ተቋማት ጉባኤ 17ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን ፕሬዝዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ በተገኙበት አካሂዷል። 

ፕሬዚዳንቱ በዚሁ ወቅት፤ ከሐይማኖታዊ መርህ ውጪ ጥላቻን የሚሰብኩ አካላት ሊታረሙ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

በኢትዮጵያ የእምነት ተቋማት የበጎነት ማሳያ እና የድሆች መጠገያ ሆነው የኖሩ ናቸው ያሉት ፕሬዝዳንት ታየ፤ ነገር ግን አንዳንዶች ኃይማኖትን ሽፋን በማድረግ ከኃይማኖታዊ መርህ ውጪ ከፍቅር ይልቅ መነጣጠል እና ጥላቻን ሲዘሩ ይስተዋላል ብለዋል።

በማኀበራዊ ሚዲያ ኃይማኖትን ሽፋን በማድረግ ጥላቻ የሚሰብኩ አካላት ሊገሰፁ እንደሚገባም ተናግረዋል።

በ17ኛው ጠቅላላ ጉባኤም ይህንኑ ድርጊት ትኩረት ሰጥቶ ማጤን ያስፈልጋል ብለዋል።

በተጨማሪም የኃይማኖት ተቋማት በሀገራዊ ምክክሩ ላይ ሚናቸውን በመወጣት ለኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም መሰረት ሊጥሉ ይገባል ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

በመድረኩ የኃይማኖት ተቋማት የበላይ ጠባቂዎች፣ የኃይማኖት አባቶች እና ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

#EBC

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...