ወራቤ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከሀበሺስታን ዴቬሎፕመንት ኤንድ ኮኦፕሬሽን ጋር በመተባበር ከነሀሴ 20 ጀምሮ ሲሰጥ የቆየው የነፃ የአይን ምርመራ እና የአይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ህክምና አገልግሎት ለ228 ዜጎች የአይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ-ህክምና በማድረግ ብርሃናቸውን በመመለስ መጠናቀቁን የሆስፒታሉ የህዝብ ግንኙነት እና ኮሙኒኬሽን ሃላፊ የሆኑት አቶ አብዱልጀባር አብደላ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል ።
የወራቤ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለ4ሺ 5መቶ 52 ዜጎች የአይን ምርመራው መደረጉንና የአይን ሞራ ግርዶሽ ያለባቸውን 228 ዜጎች በመለየት ቀዶ ህክምና እና የመድኃኒት እደላ መደረጉ ተገልጿል ።
አገልግሎቱ የተሰጣቸው ዜጎች ከተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች እንደመጡ በመጠቆምም በርካቶች በአይን ሞራ ግርዶሽ ምክንያት የአይን ብርሃናቸውን አጥተው እንደሚኖሩ ተገልጿል።
የአይን ሞራ ግርዶሽ ሳይታከም ከቆየ ለአይነ ስውርነት የሚያጋልጥ ሲሆን በጊዜ ከታከመ የሚድን በመሆኑ ችግሩ ያለባቸው አካላት ምርመራ ማድረግና መታከም እንዳለባቸውም አቶ አብዱልጀባር አብደላ አክለው ገልጸዋል።
