የሲኖትራክ ተሽከርካሪዎች ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገቡ ከተከለከለ ከአራት ወራት በኃላ፣ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ኩባንያው የቴክኒክ ችግር ያለባቸውን መኪኖች በተለይም ገልባጮችን ስታንዳርዳቸውን ለማሟላት የማስተካከል ሥራ መጀመሩን አረጋግጫለሁ ብለዋል።
ሚኒስትር ዴኤታው ባረኦ ሀሰን ፤ ከዚህ ቀደም በተደረገ ጥናት በፍሬናቸው አካባቢ በነበሩ የቴክኒክ ጉድለቶች ምክንያት የትራፊክ አደጋ ሲያደርሱ የነበሩት ተሽከርካሪዎች፣ ኩባንያው ችግሮቹን ለማስተካከል በገባው ቃል መሠረት ሥራው መጀመሩን አስታውቀዋል።
የቻይናው የጭነት መኪና አምራች ኩባንያ ሊያሟላቸው የተስማማባቸው እና ከዚህ ቀደም ተሽከርካሪዎቹ የጎደሏቸው የነበሩት ክፍሎችን ማለትም የውስጥ እና የውጪ 360 ዲግሪ የሚያሳዩ ካሜራዎች
የፍሬን ጥንካሬ ማሻሻያ ፣ ከተፈቀደ ክብደት በላይ ሲጫን የሚያሳውቅ ማንቂያ እና ሌሎች ክፍሎች ይገኙበታል።
ይህን የማስተካከያ ሥራ ያስከተለው እገዳ መጀመሪያ የተጣለው በግንቦት 27 ቀን 2017 ዓ.ም. መሆኑን ይታወሳል።
CapitalNews
