ከአንድ ሺሕ በላይ ግለሰቦች በኃይል ማጭበርበር ተጠየቁ

Date:


በ2017 ‎በጀት ዓመት ከ 3 ነጥብ 1 ሚሊዮን በላይ በሚሆኑ የኢነርጂ ቆጣሪዎች ላይ ምርመራ ተድርጎ ከአንድ ሺህ በላይ ግለሰቦች የማጭበርበር ተግባር ሲፈጽሙ መገኘታቸውን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታውቋል።

‎መሥሪያ ቤቱ በበጀት ዓመቱ ከ2 ነጥብ 2 ሚሊዮን በላይ የኢነርጂ ቆጣሪዎችን ቤት ለቤት ምርመራ ለማድረግ አቅዶ ከ 3 ነጥብ 1 ሚሊዮን በላይ በሚሆኑት ላይ ምርመራ ማድረጉን የገለጸ ሲሆን፤ በዚህም ከአንድ ሺሕ በላይ ግለሰቦች የማጭበርበር ተግባር መፈፀማቸውን ተከትሎ በሕግ ተጠያቂ ማድረግ ተችሏል ተብሏል።

‎ነባር የኢነርጂ ቆጣሪዎችን በዘመናዊ ስማርት ቆጣሪዎች የመተካት ሥራ እየተሰራ መሆኑን የገለጹት የአገልግሎቱ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢንጂነር ጌቱ ገረመው፤ ከ53 ሺሕ 700 በላይ ስማርት ቆጣሪዎችን ወደ አገልግሎት ማስገባት መቻሉንም ተናግረዋል።

‎በተጨማሪም ወርሃዊ የኢነርጂ የፍጆታ ሃሳባቸውን በተለያዩ ዘመናዊ የክፍያ አማራጮች የሚከፍሉ ደንበኞች ቁጥር ከ94 በመቶ በላይ ማድረስ የተቻለ ቢሆንም፤ ከታክስ ክፍያ ጋር በተያያዘ በርካታ ጥያቄ እንደቀረቡ አስረድተዋል።

‎ተቋሙ በ2017 በጀት ዓመት ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የገዛው የኢነርጂ መጠን ከ16 ሺሕ 240 በላይ ጊጋ ዋት ኢነርጂ መሆኑን የገለጹም ሲሆን፤ ለ2018 በጀት አመት ከ18 ሺህ 230 በላይ ጊጋ ዋት ኢነርጂ በመግዛት ለተገልጋዮች ለማሰራጨት ማቀዱንም አስታውቋል።

በአጠቃላይም ‎በበጀት ዓመቱ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በዕቅድ ካስቀመጠው 96 በመቶ የሚሆነውን በማሳካት፤ 63 ነጥብ 12 ቢሊዮን ብር መሰብሰቡን ተናግረዋል።

“ይህም የ2017 እቅድ አፍፃፀም ከ2016 በጀት ዓመት ጋር ሲነፃፀር ከ48 በመቶ በላይ የገቢ እድገት ተመዝግቧል” ብለዋል።

‎ገቢው የተገኘው ከኢነርጂ ሽያጭ፤ ከምሶሶ ሊዝ፤ ከማማከር አገልግሎት እንዲሁም፤ የማያገለግሉ ንብረቶችን በሽያጭ በማስወገድ በአጠቃላይ በ2017 በጀት አመት 63 ነጥብ 12 ቢሊዮን ብር ገቢ መገኘቱን ኢንጂነር ጌቱ ገልጸዋል።

‎”የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በገጠር ከተሞችን የኤሌክትርክ ተጠቃሚ ለማድረግ ከ100 በላይ ኪ.ሜ የመካከለኛ መስመር፤ ከ131 ኪ.ሜ የዝቅተኛ መስመር እንዲሁም 4 ሺሕ 97 ምሰሶዎችን እና ማስተላለፊያዎችን (ትራንስፎርመሮች)ን የተከላ ሥራ አከናውኗል” ብለዋል፡፡        

‌‎በተጨማሪም የ2017 በጀት ዓመትን ጨምሮ አጠቃላይ 5 ነጥብ 21 ሚሊዮን ደንበኞችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉንም የአገልግሎቱ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢንጂነር ጌቱ ገረመው ገልጸዋል።

‎በቀጣይ አዳዲስ 800 ሺሕ ደንበኞችን የኤሌክትሪክ አገልግሎት እንዲያገኙ ለማድረግ እንደሚሰራ ተጠቁሟል።

(አሐዱ ሬዲዮ)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...