ንጉስ ማልት በምርት ጥራት ተሸለመ

Date:

በምርቱ ጣዕም እና ጥራት ተወዳጅነትን ያተረፈው ንጉስ ማልት ለሽልማት በቅቷል።

ሸላሚው  ድርጅት በ1961 በብራስልስ፣ ቤልጂየም የተመሰረተው Monde Selection ሲሆን ግንባር ቀደም ራሱን የቻለ የጥራት ግምገማ ተቋም ነው።

በጠንካራ ግምገማዎቹ እና መስፈርቶቹ የሚታወቀው ሞንዴ ሰሌክሽን በየአመቱ ምርቶችን በምግብ፣ መጠጦች፣ መዋቢያዎች እና ሌሎችንም ከ3,000 በላይ የሆኑ የተለያዩ  ምርቶች ገምግሞ እንደየ ጥራት ደረጃቸው ሽልማት ይሰጣል።

ይህ ተቋም የነሐስ፣ ሲልቨር፣ ወርቅ እና ግራንድ ወርቅን ጨምሮ የተከበሩ የጥራት መለያዎችን በመሸለም በአለም አቀፍ ደረጃ ይታወቃል።

ከ60 ዓመታት በላይ ባለው እውቀት፣ Monde Selection በተጠቃሚ ምርቶች ጥራት ላይ ዓለም አቀፍ ደረጃዎችን ያዘጋጃል።

በእዚህ ትልቅ ተቋም ከአልኮል ነፃ መጠጥ የሆነው ንጉስ ማልት የ2025 በምርት ጥራት የወርቅ ተሸላሚ ሆኗል።

ንጉስ ማልት ከሞድን ሰሌክሽ የጥራት ሽልማት ሲያገኝ ይህ የመጀመሪያው አይደለም።

ባለፈው አመትም የብር ተሸላሚ እንደነበር ይታወሳል። በአገራችን ኢትዮጵያ ከንጉስ ተጨማሪም ሌሎች ምርቶችም እንደየ ጥራት ደረጃቸው እውቅና እና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

ይህ ተደጋጋሚ ሽልማት ለንጉስ ማልት እና ለተጠቃሚዎቹ ብቻ ሳይሆን ለአገር  የሚያበረክተው እውቅና ቀላል አይደለም።

ንጉስ ደረጃውን አስጠብቆ እንዲቆይ ለሌሎች ምርቶች ደግሞ  አርአያ በመሆን በምርት ጥራታቸውን አስጠብቀው ከአመት አመት ለሽልማት እንዲበቁ መነቃቃትን ይፈጥራል ።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...