የፌዴራል የገቢ ግብር አዋጅን ለማሻሻል በወጣ አዋጅ ቁጥር 1395/2017 መሰረት ከዲጂታል ይዘት ፈጠራ የሚገኝ ገቢ ምን ማለት እንደሆነ ያስቀምጣል።
ይህም አንድ ግለሰብ ወይም ድርጅት የቪዲዮ ማጋሪያ አገልግሎቶችን፣ የማህበራዊ ሚዲያ መድረኮችን፣ የድምጽ ማስተላለፊያ (ፖድካስት) አገልግሎቶችን እና የቀጥታ ስርጭት መድረኮችን ጨምሮ በኦንላይን መድረኮች ላይ ዲጂታል ይዘትን በመፍጠር እና በማሰራጨት የሚያገኘው ማንኛውም የገንዘብ ወይም በአይነት የሚገኝ ገቢ እንደሆነ ይገልጻል።
ይህም የሚከተሉትን ገቢዎች ያካትታል፦
° ማስታወቂያዎች እና ስፖንሰርሺፖች፤
° የምርት ስም ስምምነቶች እና ድጋፎች፤
° የአጋርነት ግብይት እና የምርት ምደባዎች፤
° የደጋፊዎች አስተዋጽኦ፤
° የገንዘብ ስጦታዎች ወይም የብዙሃን የገንዘብ ማሰባሰብ (ክራውድ ፈንዲንግ)፤
° የአባልነት ክፍያዎች፤
° የዲጂታል ወይም የአካላዊ ሸቀጦች ሽያጭ፤
° ለማስተዋወቂያ እንቅስቃሴ ምትክ የተገኙ ዕቃዎች ወይም አገልግሎቶች፤
° ከዚህ በላይ ከተጠቀሱት ጋር ተመሳሳይነት ያላቸው ሌሎች ክፍያዎች ናቸው።
የገቢዎች ሚኒስቴር
