ወወክማ እና ካቦድ ከ500 በላይ ወጣቶች የክረምት ሥልጠና ለመስጠት ስምምነት ተፈራረሙ

Date:

የኢትዮጵያውያን ወጣቶች ወንዶች ክርስቲያናዊ ማኅበር (ወወክማ) ከካቦድ ማርኬቲንግ ሶሉሽን ጋር የሥራ ዕድል ስምምነት ተፈራረመ።

ተቋማቱ በመጪው ክረምት ከ500 ለሚበልጡ ወጣቶች ሥልጠና ለመስጠት በጋራ ይሠራሉ ተብሏል። ሁለቱ ተቋማት ሰኔ 16 ቀን 2018 ዓ.ም. በሰጡት የጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ ስምምነቱን ይፋ አድርገዋል።

ወጣቶቹ ስልጠናውን የሚወስዱት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር እንደሆነ በጋዜጣዊ መግለጫው ተገልጿል።
የማኅበሩ ዋና ዳይሬክተር አቶ በፍቃዱ በዛብህ ድርጅቱ በወጣቶች ላይ ትኩረት አድርጎ እንደሚንቀሳቀስ ጠቅሰው፤ በአጠቃላይ ማኅበረሰቡ ላይ ለውጥ ለማምጣት የሚሠራ የበጎ አድራጎት ድርጅት መሆኑን አንስተዋል።

አዲሱ አሠራር በኢትዮጵያ የሚታየውን የሥራ አጥነት ችግር ለማቃለል ትልቅ አስተዋጽኦ አለው። በዘርፉ የሚታዩትን ማነቆዎች ለመፍታትም ሚናው የጎላ እንደሆነ ዋና ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል።

ማኅበሩ ከዚህ ቀደም በተለይም የዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን የሚያጠናቅቁ ወጣቶች በፍጥነት ስራ እንዲያገኙ እና ስራ መቀጠር የሚያችላቸውን ክህሎት እንዲይዙ እገዛ እያደረገ እንደሆነ አቶ በፍቃዱ ገልጸዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለ10 ምሁራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጥቷል

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ቦርድ ጥቅምት 12 ቀን 2019...

ዳሸን ባንክ እና ሼባ ማይልስ የፕላቲንየም ብራንድ የማስተር ካርድ ይፋ አደረጉ

ዳሸን ባንክ እና ሼባ ማይልስ በኢትዮጵያ ለሚገኙ ደንበኞች የፕሪሚየም...

የአሜሪካ የደህንነት ኃላፊ ኢራንን አስጠነቀቁ

ቡሔራዊ ደህንነት ዳይሬክተር ጄይ ክላይተን አርብ ዕለት ኢራን በውጭ...

ኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ  በአመት ከ1.1 ቢሊዮን ዶላር በላይ ታጣለች

85 በመቶ የሚሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ በግብርናው ዘርፍ የተሰማራ ሲሆን...