ውድ የባንካችን ደንበኞች የጥንቃቄ መልዕክት አለን!

Date:

ማንኛውንም በስልክ የሚመጣ ጥያቄ ባለመቀበል እራሳችሁን ከአጭበርባሪዎች ጠብቁ!!!

ባንካችን ብ
ሔራዊ ባንክ ያወጣውን መመሪያ መሰረት በማድረግ ደንበኞቻችን በአቅራቢያቸው ወደሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ በመሄድ የባንክ ሒሳብ ቁጥራቸውን ከፋይዳ መታወቂያቸው ጋር እንዲያጣምሩ ያስተላለፈውን  መልእክት እንደ አጋጣሚ በመጠቀም አጭበርባሪዎች ደንበኞቻችን ጋር እየደወሉ አገልግሎቱ በስልክ እንደሚሰጥ እንዲሁም የባንክ ሂሳብ በዚህ ምክንያት እንደሚዘጋ በማስመሰል ለማጭበርበር እየተጠቀሙበት እንደሚገኙ ደርሰንበታል።

በመሆኑም ክቡራን ደንበኞቻችን ሒሳብን ከፋይዳ መታወቂያ ጋር የማጣመሩ ሥራም ሆነ ሌሎች ከሞባይል ባንኪንግ ጋር የተያያዙ እና ማናቸውም አገልግሎቶች እርስዎ በአካል ወደ ቅርንጫፍ ካልሄዱ/ካልቀረቡ በስተቀር በስልክ ተደውሎ የማይሰጥ መሆኑን አውቃችሁ በስልክ ለሚመጡ ጥያቄዎች ምላሽ ባለመስጠት እራሳችሁን ከአጭበርባሪዎች እንድትጠብቁ በአክብሮት እናሳውቃለን!


የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ!

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...