የኃይል አቅርቦትን ለማሻሻል የ4.3 ቢሊዮን ብር ፕሮጀክት ተጀመረ

Date:

በአዲስ አበባ እና በሸገር ከተሞች የሚታየውን የኤሌክትሪክ መቆራረጥ በ27 በመቶ የሚቀንስ የ4.3 ቢሊዮን ብር ግዙፍ የኃይል ማሻሻያ ፕሮጀክት እየተከናወነ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት እንዳስታወቀው፣ ከዓለም ባንክ በተገኘ ብድር የሚተገበረው ይህ የአዴሌ (ADELE) ፕሮጀክት በአሁኑ ወቅት 36.74 በመቶ አፈፃፀም ላይ ደርሷል።

ሥራው 703 ኪሎ ሜትር የኔትዎርክ መስመር ዝርጋታን፣ የ2 ሺህ አዳዲስ ትራንስፎርመሮችን ተከላ እና የሌሎች 2 ሺህ ነባር ትራንስፎርመሮችን አቅም የማሳደግ ተግባራትን ያካትታል።

በኮንክሪት ምሰሶና በሽፍን ኬብል የሚከናወነው ይህ ግንባታ የትራንስፎርመር መቃጠል አደጋን በእጅጉ የሚቀንስ ሲሆን፣ አስተማማኝና ቀጣይነት ያለው የኃይል አቅርቦት ለነዋሪዎች ለማድረስ ያለመ እንደሆነ ተገልጿል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...