የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከደቡብ ኮሪያ ጋር የ15 በመቶ የታሪፍ ጭማሪ ላይ ስለመስማማታቸው ተናገሩ።
ዶናልድ ትራምፕ ከደቡብ ኮሪያ ጋር ሙሉ ለሙሉ የንግድ ስምምነት መድረሳችንን ላሳውቅ እወዳለሁ ሲሉ በትሩዝ ማህበራዊ ትስስር ገፃቸው አስታውቀዋል።
የደቡብ ኮሪያው ፕሬዝዳንት ሊ ጄ ያንግ በበኩላቸው ስምምነቱ ሀገራችንን ከሌሎች ሀገራት እኩል ወይም በተሻለ ደረጃ ላይ ያስቀምጣታል ብለዋል።
ስምምነቱ አሜሪካ በርካታ ሀገራት ከዋሺንግተን ጋር የንግድ ስምምነት ላይ እንዲደርሱ ካስቀመጠችው ቀነ ገደብ ዋዜማ ላይ የተደረገ ነው ተብሏል።
የዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር በርካታ ሀገራት ከነሀሴ አንድ አስቀድሞ የንግድ ስምምነት ከአሜሪካ ጋር እንዲደርሱ አለበለዚያ ከፍተኛ የታሪፍ ጭማሪ እንደሚጠብቃቸው ማሳሰቧ ይታወሳል።
ስምምነቱ ባይፈፀም የ25 በመቶ የታሪፍ ጭማሪ ደቡብ ኮሪያ ይጠብቃት ነበር ተብሏል።
የደቡብ ኮሪያው ፕሬዝዳንት በመጪው ሁለት ሳምንት ወደ ነጩ ቤተመንግስት በማቅናት ከትራምፕ ጋር ይወያያሉ ተብሏል።
ዘገባው የቢቢሲ ነው።
