በደሴ ከተማ የሚገኘው የስሬ ምንጭ መካነ-ሕይወት መስቀለ ክርስቶስ እና አባ ጊዮርጊስ ዘ-ጋስጫ ቤተ ክርስቲያን የአብነት ትምህርት ቤት እና የሰ/ት/ቤት አዳራሽ በትናንትናው ዕለት ምክንያቱ ባልታወቀ ድንገተኛ የእሳት አደጋ ሙሉ ለሙሉ ወድሟል።
በቃጠሎውም የአብነት ተማሪዎች መገልገያ መጻሕፍት አልባሳት እና ሌሎች እቃዎች ላይ ሙሉ ለሙሉ ጉዳት የደረሰ ሲሆን በሰው ሕይወት ላይ ምንም ጉዳት አለማድረሱን ለማወቅ የተቻለ ሲሆን በአጠቃላይ ከ 2,000,000 ብር በላይ የሚያወጣ ንብረት ላይ ጉዳት መድረሱ ተመላክቷል ።
በደብሩ ከ 200 በላይ የአብነት ተማሪዎች የሚገኙ ሲሆን በአሁን ሰአት መጠለያ እና የመማሪያ ቁሳቁስ እጥረት ያጋጠማቸው በመሆኑ የአብነት ተማሪዎቹን ለመደገፍ እንዲሁም የወደመውን ሀብት ለመተካት የተቋቋመ ኮሚቴ ስራውን መጀመሩ ተገልጿል ።
ዘጋቢ:- ዲ/ን አዶንያስ ሀብታሙ
