በአውስትራሊያ ቦንዳይ በተከፈተ ተኩስ ሳቢያ ህይዎታቸዉን ያጡ ሰዎች ቁጥር 16 ደረሰ፡፡
የአይሁድ ማህበረሰብ ላይ ያነጣጠረው ጥቃት 40 ሰዎችንም አቁሰሏል ተብሏል።
የሲድኒ ፖሊስ “ሃኑካ” በተሰኘው የአይሁዳዉያን የብርሃን በዓል ላይ የደረሰዉን ጥቃት የሽብር ድርጊት ነው ብሎታል ።
ለስምንት ቀናት የሚቆይ በዐል ሲሆን በመጀመሪያው ቀን ከ1000 በላይ የሲደኒ አይሁደአዉያን በቦታው ላይ ነበሩም ተብሏል።
በሲድኒዋ ቦንዳይ ባህር ዳርቻ በተከፈተዉ ጅምላ ተኩስ የፀጥታ ዓባላት ሳይቀሩ ተገድልዋል ተብሏል።
በተፈጸመው ጥቃት ታዳጊ እና ሁለት ፖሊሶች ህይዎታቸዉ ሲያልፍ አንደኛዉ ጥቃት አድራሽም ወዲያውኑ ህይወቱን አቷል ።
ሁለተኛዉ ተጠርጣሪም እጅጉን አደገኛ በሚባል ሁኔታ ውስጥ ነዉ የሚል መረጃ ወቷል።
የኒው ሳውዝ ዌልስ ፖሊስ ጥቃት አድራሾቹ የ50 እና 24 ዓመት አባትና ልጀእ መሆናቸዉንም አሳውቋል።
የአውስትራሊያው ጠቅላይ ሚኒስትር አንቶኒ አልበአኔዝ ጥቃቱን አዉግዘዋል።
“የፀረ-ሴሚቲክ” ተግባር ነው በሚልም የጥቃቱን አስከፊነት አሰታውሰዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።
ጥቃቱ ለምን እንደደረሰ ምርመራ እየተደረገበት መሆኑንም የአገሪቱ የደህንነት ሀይሎች ይፋ አድርገዋል።
ዘገባዉ የቢቢሲና አልጀዚራ ነው።
