የደመወዝ ጥያቄ በማንሳታቸው ለእስር የሚዳረጉ ሠራተኞችን በተመለከተ አፋጣኝ እርምጃ እንደሚወስድ ገለፀ

Date:

በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች በተለይም የመምህራን እና የጤና ባለሙያዎች ደመወዝ ሳይከፈል በመቆየቱ በሠራተኞችና በአሠሪዎች መካከል ችግር ሲፈጥር ቆይቷል።

በዚህም የደመወዝና ጥቅማጥቅ ጥያቄ የሚያነሱ ሠራተኞች ለእስር መንገላታት ብሎም ሥራን እስከማሳጣት የደረሰ እርምጃ ሲወሰድባቸውም ይስተዋላል።

በማህበር የተደራጁ ሠራተኞች የተለያዩ የደመወዝ ጥያቄዎችን በማንሳታቸው የሚደርስባቸውን እስር በተመለከተ አፋጣኝ እርምጃ እንደሚወሰድ የገለጹት የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማህበራት ኮንፌደሬሽን (ኢሠማኮ) ፕሬዝዳንት ካሳሁን ፎሎ ናቸው።

ያልተደራጁ ሠራተኞች ላይ የሚደርሰውን ጥቃት በተመለከተ የሚደርሰው መረጃ መኖሩን የገለጹት ፕሬዝዳንቱ፤ “ከተለያዩ የክልል አመራሮችና የጸጥታ ኃላፊዎች ጋር በመነጋገር እስር የደረሰባቸው ሠራተኞች በሁለት እና ሦስት ቀናት ውስጥ እንዲለቁ ይደረጋል” ሲሉ ገልጸዋል።

በክልሎች ባሉ ጽህፈት ቤቶች በኩል የተደራጁ ሠራተኞች ጉዳይ በትኩረት የሚከታተል መሆኑና የሚያነሱት ጥያቄም ምላሽ ለማሰጠት እየተሰራ መሆኑን አክለዋል።

ነገር ግን የጤና ባለሙያዎች እያነሱት ያለውን ጥያቄ በተመለከተ “ከኢሰማኮ ጋር ግንኙነት የለውም ያሉ የመንግሥት ሠራተኞች የኢሰማኮ አባል አይደሉም” በማለት፤ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች አባል መሆናቸውን ጠቁመዋል።

የጤና ባለሙያዎች መረጃውን አለመስጠታቸውና ወደ ኢትዮጵያ ሠራተኛ ማህበራት ኮንፌደሬሽን አለመምጣታቸውን ገልጸዋል።

ከከፍተኛ የጤና ባለሙያ ስፔሻሊስቶች ጀምሮ ዶክተሮች፣ ነርሶች፣ እና የቀዶ ጥገና ባለሙያ የሆኑ የጤና ባለሙያዎች በተለያዩ የማህበራዊ መገናኛ ዘዴ መተግበሪያዎች፤ “ሕይወትን ስናድን ኖረናል አሁን ግን የራሳችንን ሕይወት ማዳን ይኖርብናል” በሚል መፈክር ስላሳሰባቸው ዝቅተኛ ደመወዝ ጉዳይ ጥያቄ እያነሱ መሆኑ ይታወቃል፡፡

(አሐዱ ሬዲዮ)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...