ደስታቸውን ሲገልፁ በተነሳ ግርግር 2 ሰዎች ሞተው፣ 192 ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል

Date:

ፒኤስጂ ትናንት የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግን ማሸነፉን ተከትሎ የክለቡ ደጋፊዎች በፈረንሳይ ዋና ከተማ በፓሪስ ጎዳናዎች ላይ ደስታቸውን ሲገልጹ አምሽተዋል።

በዚሁ ወቅት በተነሳ ግርግር 2 ሰዎች ሞተው 192 ደግሞ ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን፤ ከ500 በላይ ሰዎች በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለዋል።

ይህ እንዳይመጣ ተፈርቶ ከ5 ሺህ 400 በላይ ፖሊሶች በደንብ ማስከበር ሥራ ላይ ተሰማርተው የነበረ ቢሆንም፤ ደስታቸው ከቁጥጥር ውጪ የሆነባቸው ድጋፊዎች ግን በተለያዩ ቦታዎች እሳት አስነስተዋል።

በዚህም 200 ያህል መኪኖች እንደተቃጠሉ እንዲሁም የአውቶቡስ ፌርማታዎችና ሌሎች መሰረተ ልማቶች እንደተሰባበሩ ታውቋል።

ደጋፊዎቹ ከፖሊስ ጋርም ተጋጭተው የነበረ በመሆኑ፤ ፖሊስ ውሃ በመርጨት እና አስለቃሽ ጭስ በመተኮስ ለመበተን ሞክሯል።

በተነሳው ግርግር 22 ፖሊሶች እና 9 የእሳት አደጋ ሰራተኞችም ጉዳት ደርሶባቸውል።

በትናንትናው ዕለት ፓሪስ ሴንት ዠርሜን የጣሊያኑን ኢንተር ሚላን በሰፊ የጎል ልዩነት በማሸነፍ የመጀመርያውን የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫን ያነሳ ሲሆን፤ በዚህም በፓሪስ የሚገኙ ድጋፊዎቹም ደስታቸው ከቁጥጥር ውጭ ሆኖ አምሽተዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...