ዳንጎቴ በኢትዮጵያ የማዳበሪያ ፋብሪካ ለመገንባት ስምምነት አደረገ

Date:

የዳንጎቴ ቡድን በኢትዮጵያ የማዳበሪያ ፋብሪካ ለመገንባት የ3 ቢሊየን ዶላር ስትራቴጂካዊ ስምምነት ማድረጉን የቡድኑ ፕሬዝዳንት እና ዋና ሥራ አስፈፃሚ አሊኮ ዳንጎቴ አስታወቁ፡፡

ፕሬዝዳንቱ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ፤ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የማዳበሪያ ፋብሪካ በሶማሌ ክልል ጎዴ ለመገንባት ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር የ3 ቢሊየን ዶላር ስትራቴጂካዊ ስምምነት ላይ መድረሳቸውን አስታውቀዋል፡፡

ይህ ፕሮጀክት ኢንቨስትመንት ብቻ ሳይሆን፤ ኢትዮጵያ በግብርና ዘርፍ ራሷን እንድትችል እና ቀጣናዊ ኢኮኖሚያዊ ትስስር ለመፍጠር ያላትን ጠንካራ ቁርጠኝነት የሚያጠናክር ነው ብለዋል።

ፕሬዝዳንቱ እንደገለጹት፤ የአቅርቦት ችግር ያለባቸውና ከሞሮኮ እና ሩሲያ በሚመጡ ምርቶች ላይ ጥገኛ የሆኑ ሀገራት አፋጣኝ ርምጃ መውሰድ አለባቸው።

ዓላማችን የዩሪያ እና የናይትሮጅን ማዳበሪያዎችን በሀገር ውስጥ በማምረት የኢትዮጵያን ገበሬዎችን ፍላጎት ለማሟላት እና በመላው ምሥራቅ አፍሪካ እየተመዘገበ ያለውን ዕድገት ማበረታታት ነው ብለዋል፡፡

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ራዕይ እና ሀገር በቀል ኢኮኖሚያዊ ሪፎርም መሰረት ስትራቴጂካዊ ስፍራ በሆነው የኢትዮ – ጅቡቲ ድንበር ላይ የምትገኘው የጎዴ ከተማ አዲስ የኢንዱስትሪ ማዕከል እንደምትሆንም አመላክተዋል፡፡

በኢትዮጵያ በሲሚንቶ ዘርፍ ያገኘነውን ስኬት ተከትሎ ይህ አዲስ ተነሳሽነት በምሥራቅ አፍሪካ ለምናደርገው መስፋፋት ወሳኝ ርምጃ ነውም ሲሉም በጽሁፋቸው ገልጸዋል፡፡

አክለውም አፍሪካ ራሷን መመገብ አለባት። በጋራ የምግብ ዋስትናን በማረጋገጥ፣ የስራ ዕድል ፈጠራን በማጠናከር የመጭውን ትውልድ መፃኢ ዕድል እንገነባለን ብለዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...