ድህነትን  ለመቀነስ  ትምህርት ላይ ትኩረት አድርጎ መስራት ያስፈልጋል

Date:

ሪች ፎር ቼንጅ ኢትዮጵያ ሶስት ዋና ዋና  አላማዎችን ይዞ እየሰራ የሚገኝ ሲሆን ከእነዚህም  ድህነትን መቀነስ ሴቶችን በኢኮኖሚ ማጎልበት እና ትምህርት ትኩረት አድርጎ እየሰራ ይገኛል ።

ድህነትን  ለመቀነስ  ትምህርት ላይ ትኩረት አድርጎ መስራት ያስፈልጋል ሲሉ የሪች ፎር ቼንጅ ካንትሪ ማናጀር የሆኑት መቅድም ጉልላት በተለይ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል። አክለውም በተለያዩ መንገድ ዌብሳይት ቀርሰው  ለሚሰሩ  እና የመማር ማስተማር ሂደቱን በበዙ መንገድ እየረዱ ላሉ እና  ለሀገር አቀፍ  ፈተና ለሚወስዱ የፈተና ልምምድ ጊዜ እንዲወስዱ እና ወጤታማ ትውልድ ለመፍጠር እየሰሩ ይገኛሉ።

የገንዘብ እጥረት ለሚያጋጥማቸው እስከ 60 ሺህ ዶላር ድጋፍ እንደሚደርግላቸው ተጠቁሟል። በተጨማሪም  ሪች ፎር ቼንጅ ኢትዮጵያ ከስዊድን ጋር ለ80 ዓመታት የዘለቀው ዲፕሎማሲያዊ  ግንኙነቷን የሚያጠናክር መሆኑን በዕለቱ ዝግጅት  የተገኙት የስዊድን ባለስልጣናት  በስራቸው ላሉ ተቋማት የስራ ሂደት እና ውጤት ተመልክተዋል።

በአሁኑ ወቅት ሪች ፎር ቼንጅ ትምህርት አጋዥ መተግበርያዎችን እና መፍትሄዎችን የፈጠሩ ወጣት ሶሻል ኢንተርፕረነሮችን አቅማቸውን የማጎልበት የገበያ ትስስር በመፍጠር እና የገንዘብ ደጋፍ በማድረግ የበኩሉን አስተዋጽኦ በማድረግ ላይ ይገኛል::

ሪች ፎር ቼንጅ ለትርፍ ያልተቋቋመ ዓለምአቀፋዊ ግብረ ሰናይ ደርጅት ሲሆን በዋናነትም በማህበረሰብ ወስጥ የሚስተዋሉ ችግሮቸን ለመፍታት የተለሙ ሥራ ፈጣሪዎችን  የሚያግዝ ግብረሰናይ ድርጅት ነዉ::

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ውጭ ምንዛሪ የሚያድኑ የሴራሚክ ምርቶች በቅርቡ ለገበያ ይቀርባሉ

ይህ የተገለፀው ኢትዮደር ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር በ”Golden Tier...

የዓለም የቡና ገበያ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ መቀነሱ ተገለጠ

በዓለም አቀፍ ደረጃ በቡና አቅርቦት ላይ ተፈጥሮ የነበረው ስጋት...

አሜሪካ የኢራንን የጭነት መርከብን መያዟን አስታወቀች

በሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል ወደ ኢራን ወደቦች የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን የዘጋችው...