በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 36ኛ ሳምንት ከሜዳው ውጪ ከሳውዝሃምተን የተጫወተው ማንችስተር ሲቲ 0 ለ 0 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይቷል።
ለሻምፒዮንስ ሊግ ተሳትፎ ብርቱ ፉክክር እያደረገ የሚገኘው ማንችስተር ሲቲ ከሊጉ በተሰናበተው ሳውዝሃምፕተን ነጥብ ጥሏል።
በሌሎች የሊጉ የዛሬ መርሐ ግብሮች ኤቨርተን ፉልሀምን 3 ለ1 ሲያሸንፍ ብሬትፎርድ ኢፕስዊች ታውንን 1 ለ 0 አሸንፏል፤ ወልቭስ ደግሞ በሜዳው በብራይተን 2 ለ 0 ተሸንፏል።
