Date:

የብሄራዊ ድህረ-ምረቃ (NGAT) መግቢያ ፈተና መጋቢት 5 እንደሚሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

ትምህርት ሚኒስቴር በ2017 ዓ.ም የሶስተኛ ዙር የNGAT አመልካቾች ምዘገባ መጠናቀቁን ተናግሯል፡፡

ፈተናው የሚሰጠው ዓርብ መጋቢት 5 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ጀምሮ መሆኑንም አሳውቋል። ተፈታኞች በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት በሚመደቡበት የፈተና ማዕከላት እንዲገኙ አሳስቧል፡፡

ተፈታኞች ወደ ፈተና ማዕከል በሚሄዱበት ወቅት ማንነታቸውን የሚገልጽ መታወቂያ መያዝ ይጠበቅባቸዋል።

ማንኛውም ተፈታኝ ፈተናው ከመጀመሩ 3 ደቂቃ በፊት በፈተና ማዕከል መገኘት እንዳለበት አሳስቡ ፡፡ የሞባይል ስልክ ይዞ በፈተና ማዕከል መገኘት ፈጽሞ የተከለከለ መሆኑን አስጠንቅቋል፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር የፈተና ማዕከላት ምደባ በምዝገባ ፕላትፎርም የሚገለጽ ሲልም ገልጻል።

ቀዳሚ ጽሑፍ
ቀጣይ ጥሑፍ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ግዮን መጽሔት በዛሬ ዕትሟ

ግዮን መጽሔት ዛሬ ቅዳሜ ነሔሴ 16 2018 ዓ.ም ገበያ...

ቱርክ ቤንያሚን ኔታንያሁ ላይ የእስር ማዘዣ አወጣች

ቱርክ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ላይ ዓለም አቀፍ...

በመቀለ የሚካሄደው የአሸንዳ በዓል የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት ተሰረዘ

በትግራይ በርካታ ታዳሚ በሚገኝበት በየዓመቱ የሚከበረው የአሸንዳ ባህላዊ በዓል...

የኢትዮጵያ ፖስታ 3 ሺሕ የሚጠጉ ቅርንጫፎቹን ወደ ባንክ ኤጀንትነት ለመቀየር እንቅስቃሴ ጀመረ

የኢትዮጵያ ፖስታ በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ 3 ሺሕ በሚጠጉ ቅርንጫፎቹ...