ግንቦት 19 ቀን 2017 ዓ.ም፣ (ሀገሬ ቴቪ)፤ ከ4 ሺህ በላይ የኮሌራ ታማሚዎች ተመዝግበው 42 ሰዎች ህይወታቸው አጥተዋል ሲል የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ፡፡
ድርጅቱ ዛሬ ባወጣው አዲስ ሪፖርት መሰረት፣ ከጥር እስከ ሚያዝያ 2017 ዓ.ም ባሉት አራት ወራት ውስጥ ጋምቤላና አማራ ክልሎች ከ 4ሺ056 በላይ የኮሌራ ታማሚዎች የተመዘገቡ ሲሆን፣ ከእነዚህ ውስጥ 42 ሰዎች በበሽታው ህይወታቸውን አጥተዋል ብሏል።
አብዛኛው የበሽታው ወረርሽኝ መጠን በአማራ ክልል ውስጥ በእጅጉ የሚጨምር መሆኑ ተገልጿል፡፡ ሪፖርት ከተደረጉት አጠቃላይ የወረርሽኝ መጠን ውስጥ 89.9 በመቶ የሚሆኑት ከአራት ወረዳዎች ብቻ የመጡ ናቸዉ ተብሏል።
ባለፉት ሰባት ቀናት ውስጥ በአማራ ክልል ተጨማሪ ሁለት ወረዳዎች አዳዲስ የኮሌራ ታማሚዎችን ሪፖርት መደረጋቸውን የአለም ጤና ድርጅት ሪፖርት ያሳያል።
