7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በስኬት እንዲጠናቀቅ የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል ተግባሩን አጠናክሮ ይቀጥላል

Date:

የኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በስኬት እንዲጠናቀቅ የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል እያደረገ ያለውን ተግባር አጠናክሮ ይቀጥላል አሉ።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በስኬት እንዲጠናቀቅ በሰው ኃይል፣ በትጥቅና በቴክኖሎጂ ያደረገውን ቅድመ ዝግጅት አስመልክቶ ለፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል ማብራሪያ ሰጥቷል።

በዚሁ ወቅት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይሉ ለምርጫው ያደረገው ዝግጅት እጅግ ጠንካራ መሆኑን ተናግረዋል።

ምርጫውን ለማደናቀፍ የሚንቀሳቀሱ ኃይሎች የተለያዩ ሙከራዎችን እያደረጉ ቢሆንም መከላከያ ሠራዊት ከሌሎች የፀጥታና ደኅንነት ኃይሎች ጋር እነዚህን የጥፋት ዕቅዶች ማክሸፉን አረጋግጠዋል።

አክለውም የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ የዜጎችን ደህንነት ለመጠበቅና በተለይም 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ከፍተኛ ድርሻ እንዳለው አመልክተዋል።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ጠቅላይ አዛዥ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል በበኩላቸው÷ የጋራ ግብረ ኃይሉ ከምርጫ ቦርድ ጋር መረጃዎችን በመለዋወጥና ከሕዝቡ ጋር በመተባበር እየሰራ ነው ብለዋል።

በዚህም በቅድመ ምርጫ የመራጮች ምዝገባ ሂደት፣ የምርጫ አስፈጻሚዎች እና የምርጫ ቁሳቁስ ስርጭት ደህንነት በተሳካ ሁኔታ መከናወኑን አንስተዋል።

ቀሪውን የምርጫ ሒደት ሰላማዊነት ለማረጋገጥ አስፈላጊ የሆነ ሎጂስቲክስና ትጥቅ መሟላቱን እንዲሁም ለተልዕኮው የሚመጥን በቂ ስልጠናና ኦሪንቴሽን የወሰደ የሰው ኃይል በሁሉም የኢትዮጵያ ክፍል መሰማራቱን ገልጸዋል።

በቀጣይ ምርጫው በስኬት እንዲጠናቀቅ በቴክኖሎጂ የታገዘ የፀጥታና ደህንነት የማስከበር ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ነው ያስገነዘቡት፡፡

ከምርጫው በኋላ የሚከናወኑ ሒደቶች በስኬት እንዲጠናቀቁ ግብረ ኃይሉ ሙሉ ዝግጅት ማድረጉንም ኮሚሽነር ጀነራሉ አረጋግጠዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...