አል አረቢያ የዜና ማሰረጫ እንደዘገበው ሁለቱ ወገኖቹ በአሁኑ ወቅት የእስራኤል ወታደሮችን መልሶ ማሠማራት በሚቻልበት መንገድ ዙሪያ እየተወያዩ ነው።
ሃማስ ከእስራኤል ጋር አዲስ የተኩስ አቁም ስምምነት ለማድረግ የቀረበለትን ጥያቄ እንደሚቀበል እና ድርድር ለመጀመር ዝግጁ መሆኑን ባለፈው ሳምንት አረጋግጧል።
👉 ይኔት የዜና አውታር ከፍተኛ የእስራኤል ምንጩን ጠቅሶ ቅዳሜ እንደዘገበው የቴል አቪቭ ባለሥልጣናት ከሃማስ ጋር በሚደረገው የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ቀጥተኛ ያልሆነ ድርድር ለማድረግ ልዑካቻውን ወደ ኳታር ለመላክ ወስነዋል።
