በአሜሪካን ሀገር የተሰራው “ሊያ” ፊልም ሊመረቅ ነው

Date:

በተዋናይት ደራሲና ፕሮዲዩሰር ቅድስ ባየልኝ ተጽፎ የተዘጋጀው “ሊያ” ፊልም ሊመረቅ ነው፡፡

በፊልሙ ላይ ተወዳጅና አንጋፋ የሆኑት ተዋናይ ወለላ አሰፋ፣ ግሩም ኤርሚያስ፤ ቅድስት ባየልኝ፣ ዲጄ ሉና እና ሌሎች እንደተሳተፉበት ተገልጿል።

የኢትዮ ውድ ኢንተርቴይመንት የኢትዮጵያ ተወካይ የፊልሙ ረዳት ዳይሬክተር ፊልሙን ሰርቶ ለማጠናቀቅ ሶስት አመት የፈጀ መሆኑን እና  በወጪ ደረጃ ከ35 ሺ በላይ የአሜሪካን ዶላር መፍጀቱን ገልጿል።

ፊልሙ የፊታችን ሀምሌ 10/2017 ዓ/ም ከምሽቱ 12:00 ሰዓት በአለም ሲኒማ በታላቅ ድምቀት እንደሚመረቅ ሀምሌ 3/2017 ዓ/ም በግዮን ሆቴል በተሰጠ መግለጫ ተነግሯል፡፡

ፊልሙን በመጻፍ እና በማዘጋጀት የተሳተፈችው ቅድስ ባየልኝ  ከዚህ ቀደም ህይወት እንደዋዛ፣ እጸበለስና ከአትላንቲክ ባሻገር የተሰኙ ፊልሞችን በመድረስ፣ በመተወንና በማዘጋጀት ተሳትፎ ማድረጓ ይታወሳል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የተፈናቀሉ ዜጎች በተጠለሉበት አካባቢ በቋሚነት መኖር የሚያስችላቸው 

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን የዳሰነች ወረዳ ከበኦሞ...

ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ 11ኛውን የኃይሌ ሆቴልና ሪዞርት በደብረ ብርሃን ከተማ አስመረቀ

ታዋቂው አትሌትና ባለሀብት ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ፣ በደብረ ብርሃን ከተማ...

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር የተዘጋጀው የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል ስቴት ኤግዘቢሽን ተከፈተ

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር አዘጋጅነት የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል...

በሊባኖስ እና በእሰራኤል የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት ተራዘመ

ትራምፕ በሊባኖስ እና በእሰራኤል መካከል የተደረሰው የተኩስ አቁም በሦስት...