አድማስ ዩኒቨርስቲ ከ6ሺህ በላይ ተማሪዎች አስመረቀ

Date:

አድማስ ዩኒቨርስቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን ከ6ሺህ በላይ ተማሪዎች በሚሊኒየም አዳራሽ አስመርቋል።

በምረቃ ሥነሥርዓቱ ለይ ንግግር ያደረጉት የዩኒቨርሲቱው ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሞላ ፀጋዬ ፤ ዩኒቨርስቲው ባለፉት 26ዓመታት በመደበኛና  በርቀት ትምህርት በድግሪ ፣በዲፕሎማና በሰርተፍኬት በርካታ ተማሪዎችን  በማሰልጠን ማስመረቁን  ተናግረዋል ።

ዩኒቨርሲቲው በሃገሪቱ የልማት እንቅስቃሴ ውስጥ የሚፈለገው የተማረ  የሰው ሃይል አሰልጥኖ በማቅረብ የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ እንደሚገኝ ፕሬዝዳንቱ ገልጸዋል ።

በዛሬው እለት ከ6 ሺህ በላይ ተማሪዎችን ያስመረቀው አድማስ ዩኒቨርሲቲ  ካስመረቃቸው  ተማሪዎች  መካከል 71 በመቶ የሚሆኑት ሴቶች መሆናቸው ተገልጿል ።

አድማስ ዩኒቨርስቲ ከኢትዮጵያ በተጨማሪ በሶማሌላንድና ፑንትላንድ ቅርንጫፍ ከፍቶ እያስተማረ እንደሚገኝ ተጠቁሟል።

ተመራቂ  ተማሪዎች በሠለጠኑበት የሞያ መስክ ሀገራቸውንና ህዝባቸውን በታማኝነትና በቅንነት ማገልገል እንዳለባቸው መልዕክት ተላልፏል ።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...