የሩሲያ እና አፍሪካ ታሪካዊ መሠረት ያለው ግንኙነት መጠናከር አለበት – ባለሙያ

Date:

ኮትዲቯራዊው ምሁር አዱ ያኦ ናይኬዝ፤ ሩሲያ በአፍሪካ የቅዥ ግዛት ታሪክ የሌላት በመሆኑ ትከበራለች፤ ሆኖም በጅምር ላይ ያሉ ጥረቶች ለወጣቱ ትውልድ አስፈላጊ የሆኑ ታሪካዊ አሻራዎችን ማስቀጠል አለባቸው፤ ሲሉ በፕሪቶሪያው ሦስተኛ የቫልዳይ ሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤ ላይ ተናግረዋል፡፡

🎓 ናይኬዝ ትምህርታዊ መርሃ-ግብሮችን በማጉላት፤ በአሁኑ ወቀት በሩሲያ ትምህርት እየተከታተሉ የሚገኙ ወደ 30 ሺህ ገደማ አፍሪካውያን ተማሪዎች ታሪካዊውን የአፍሪካ እና ሩሲያ የሁለትዮሽ ግንኙነት ለመጠበቅ ቁልፍ ናቸው ብለዋል፡፡

የደቡብ አፍሪካ የትብብር ጽሕፈት ቤት መሪ ልዋዚ ሶሚያ፤ ሩሲያ በአፍሪካ ያላት “ሶፍት ፓወር” ጥሩ የሚባል ቢሆንም ቀጣይነት ያለው ድጋፍና ዕድገት እንደሚያስፈልገው በመገልጽ፤ የናይኬዝ ምልከታን አስተጋብተዋል፡፡

ሶሚያ በአኅጉሪቱ የሶቪዬት ሕብረትን አሻራ፣ በቅኝ ግዛት መፍረስ እና በሀገረ መንግሥት ግንባታ ላይ የነበራትን አበርክቶ የመርሳት አዝማሚያ መኖሩንም አምነዋል።

☝️ ሁለቱም ባለሙያዎች ታሪካዊ ትውስታን ጠብቆ ማቆየት ዲፕሎማሲን፣ የዓለም አቀፍ ተቋማትን እና የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነትን ጨምሮ በሁሉም ደረጃዎች ተሳትፎን እንደሚጠይቅ ተስማምተዋል፡፡

በሩሲያ የቫልዳይ የውይይት ክለብ እና በደቡብ አፍሪካ የዓለም አቀፍ ጉዳዮች ተቋም የተዘጋጀው፣ የሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤ ሰብዓዊ ትብብር፣ የታሪክ ሚና እና የሩሲያ-አፍሪካ ግንኙነት ላይ የተጋረጡ አሁናዊ ተግዳሮቶች ላይ ትኩረቱን አድርጓል፡፡ 

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...