በጊቤ  ሸለቆ ብሄራዊ ፓርክ የሚደረጉ ህገወጥ የአደን ድርጊቶች አሁንም አልቆመም

Date:

ከጉራጌ ዞን መዲና ወልቂጤ ከተማ 20 ኪ.ሜ እርቀት ላይ የሚገኘው ጊቤ ሸለቆ ብሄራዊ ፓርክ አሁንም ከፈታናዎች አለመላቀቁን ተገለጸ፡፡

ከሀገሪቱ ዋና ከተማ ከአዲስ አበባ 178 ኪ.ሜ እርቀት ላይ የሚገኘው ፓርኩ፤ ማግኘት ያለበትን ያህል ትኩረት ያልተሰጠው ብሄራዊ ፓርክ ነው፡፡

የሀገር ሀብት የሆነው ፓርኩ፤ በቅርብ እርቀት ላይ የሚገኝ ቢሆንም፤ የፌደራል መንግስቱ በትኩረት ያሉበትን ፈተናዎች ለመቅረፍ ተደጋጋሚ ጊዜ ቢነሳም አሁን ከፈተና አለመላቀቁ ይገለጻል፡፡

ሰፊና በውስጡ የተለያዩ አእዋፍትና እንስሳት ያሉት፤ በተፈጥሮ የታደለ ፀጋዎች የያዘ ፓርክ ነው፡፡ ከፍተኛ የቱሪስት ማዕከል ሊሆን የሚገባ ቢሆንም ወደ ፓርኩ ለጉብኝት የሚሄዱ ቱርስቶችም፤ እንደ ፓርኩ ታሪክና ቅርበት ግን ዝቅተኛ መሆኑ ይነሳል፡፡

ቀደም ሲል የፓርኩ አያያዝ እና ደህንነት በተመለከተ GNN ተከታታይ ዘገባዎች ሲሰራ ቆይቷል፡፡ ፓርኩ ላይ የተጋረጡ አደጋዎችና ዝርዝር ፈተናዎች ሚድያችን ሲያነሳ ነበር፡፡

ህገወጥ ሰፈራ፣ ህገወጥ የደን ጭፍጨፋ፣ ህገወጥ አደን እና ሌሎች ፈተናዎች ፓርኩ ውስጥ ከሚታዩ ፈተናዎች በሚል በተለያየ ሁኔታ ተነስቷል፡፡

አዲሱ ክልል ከተመሰረተ በኋላ በክልሉ አመራሮች ዘንድ የፓርኩ ፈተናዎች በዝርዝር መነሳቱን GNN ሲዘግብ ቆይቷል፡፡ ከተወሰዱ እርምጃዎች አንዱ ፓርኩ በአዲስ አመራር እንደመራ ነበር፡፡ በዚህም አንዳንድ የመነቃቃት ምልክቶች የታዩ ቢሆን በዘላቂነት የፓርኩ ችግሮች የሚፈቱ ግን አይደሉም፡፡

ቀደም ሲል የነበሩ ችግሮች አሁንም አሉ ይላል የGNN ምንጮች፤ በፓርኩ ዙርያ ህገወጥ ሰፈራ አለ በዚህ ጉዳይ የተወሰደ ዘላቂ መፍትሄ የለም ተብሏል፡፡ እነዚህ ህገወጥ ሰፋሪዎች የሚጠቀበት እንጨትና ሌሎች ነገሮች ከፓርኩ ነው የሚጠቀሙት ነው የተባለው፡፡

ፓርኩ ሰፊ ስለሆነ የሚደረግለት ጥበቃና እንከብካቤ ወሳኝ ቢሆንም በውስጡ ሰዎች እንደ ፈለጉ ሲዘዋወሩ የፈለጉትን ሲያደረጉ ይታያሉ ተብሏል፡፡

በዋናነት በፓርኩ ውስጥ የሚገኙ ብርቅዬ እንስሳት ላይ የተደቀነው ፈተና አለ ያሉት ምንጮች፤ ህገወጥ አደን ነው፤ አዳኞች ሆን ብለው ለአደን የሚሄዱ አሉ ይህን ለማስቆም የሚሰሩ ሰራዎች ስለሌለ የፓርኩ ፈተና ሆኖ ቀጥሏል ይላሉ፡፡

ወደ ፓርኩ የሚሄዱ ቱሪስቶችና ጎብኚዎች ቀደም ሲል ከነበረው አሁን የተሻለ ቢሆንም፤ በቂ የሚባል አይደልም ተብሏል፡፡ ፓርኩ ከጉብኝት ባሻገር፤ ለምርምርና ለጥናት የሚያገለግል መሆኑ ይነገራል።

በዚህም ወልቂጤ ዩኒቨርስቲ የተወሰኑ ጥረቶች ሲያደረግ መታየቱም ይነሳል፡፡ ከአካባቢው አልፎ ለሀገር በአለም አቀፍ ደረጃ መታወቅ የሚችል፤ ገቢንና ሌሎች ግበዓቶች ማምጣት የሚችለው ጊቤ ሸለቆ ብሄራዊ ፓርክ በትኩረት ማነስ ምክንያት አሁንም ከነችግሩ ይገኛል ተብሏል፡፡

ወልቂጤ (GNN)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የተፈናቀሉ ዜጎች በተጠለሉበት አካባቢ በቋሚነት መኖር የሚያስችላቸው 

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን የዳሰነች ወረዳ ከበኦሞ...

ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ 11ኛውን የኃይሌ ሆቴልና ሪዞርት በደብረ ብርሃን ከተማ አስመረቀ

ታዋቂው አትሌትና ባለሀብት ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ፣ በደብረ ብርሃን ከተማ...

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር የተዘጋጀው የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል ስቴት ኤግዘቢሽን ተከፈተ

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር አዘጋጅነት የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል...

በሊባኖስ እና በእሰራኤል የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት ተራዘመ

ትራምፕ በሊባኖስ እና በእሰራኤል መካከል የተደረሰው የተኩስ አቁም በሦስት...