የቀድሞው የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እና በዓለም የንግድ ድርጅት (ጄኔቫ) የአፍሪካ ሕብረት ቋሚ መልዕክተኛ ሆነው ተሹመዋል።
ኢትዮጵያ የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ማህሙድ አሊ ዩሱፍ ዶ/ር ግርማ አመንቴን ለዚህ ትልቅ ኃላፊነት ለመሾም ያሳለፉትን ውሳኔ በአድናቆት እንደምትመለከተው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል።
ውሳኔው ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ መድረኮች አፍሪካን በመወከል ለምትጫወተው ሚና ሕብረቱ ያለውን ትልቅ ግምት የሚያመላክት ነው ሲል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለኢቢሲ ገልጿል።
ዶ/ር ግርማ አመንቴ የካበተ የአመራር ልምዳቸውን በመጠቀም የተጣለባቸውን ትልቅ ኃላፊነት በላቀ ብቃት እንደሚወጡት ያለውን ሙሉ እምነትም ሚኒስቴሩ ጨምሮ ገልጿል።
