በኢንዱስትሪ ፓርኮች እና ፋብሪካዎች ሰራተኞች የትርፍ ሰአት ተገደዉ ይሰራሉ

Date:

በመንግሥት አካላት መደረግ ያለበት ቁጥጥርና ክትትል አነስተኛ መሆኑን ኢሰመኮ ገለፀ። 

የኢትዩጵያ ሰብአዊ መብት ኮምሽን በአዲስ አበባ÷ በኦሮሚያ ክልል በሚገኙ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ክትትል ማድረጉን በሪፖርቱ ገልፆል።

አዲስ አበባ ከተማ፣ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ በሚገኘው የቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ  ፓርክ ውስጥ እና በኦሮሚያ ክልል፣ ሸገር ከተማ ዓለም ገና ክፍለ ከተማ በሚገኙ 10  ፋብሪካዎች ክትትል ተደርጎባቸዋል።

በተወሰኑ ድርጅቶች ሠራተኞች በቀን ከ8 ሰዓት በላይ እንዲሠሩ ቢደረግም የትርፍ ሰዓት ሥራ ክፍያ የማይፈጸምላቸው መሆኑ ተረጋግጧል።

ነፍሰጡሮችን ጨምሮ ሠራተኞችን የትርፍ ሰዓት ሥራ ተገደው እንዲሠሩ የሚደረግ መሆኑ ኢሰመኮ አረጋግጫለሁ ብሏል።

በአብዛኞቹ ፋብሪካዎች የሠራተኞች ማኅበር አለመመሥረቱ፤ ወጥ የቅሬታ ማቅረቢያ አሠራር አለመኖሩ፤ የሥራ ላይ ደኅንነትን እና የሥነ ተዋልዶ ጤናን የተመለከቱ ስልጠናዎች በበቂ ሁኔታ የማይሰጡ መሆኑ  በሪፖርቱ አመልክቷል።

ኢሰመኮ  በአዳማና እና በሃዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ የሚሠሩ ሠራተኞች የጡረታ መለያ ቁጥር በተገቢው ጊዜ ማግኘት የሚችሉበት አሠራር አለመዘርጋቱ በተጨማሪ ክትትል አረጋግጫለሁ ብሏል።

በክትትሉ ከተለዩት ችግሮች የተወሰኑት በሁሉም ሠራተኞች መብቶች ጥበቃ ላይ ተጽዕኖ ያላቸው ቢሆንም በሴት ሠራተኞች ላይ የሚያደርሱት ጉዳት ከፍተኛ ነው ተብሏል ።

በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ የሚሰሩ ሴት ሰራተኞች የሚከፈላቸው ደመወዝ ኑሮን ለማሸነፍ ስላላስቻላቸው ማታ ማታ በወሲብ ንግድ የተሰማሩ መኖራቸውን በጥናት መለየቱን የጨርቃ ጨርቅ ፌዴሬሽን መናገሩ ይታወሳል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የተፈናቀሉ ዜጎች በተጠለሉበት አካባቢ በቋሚነት መኖር የሚያስችላቸው 

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን የዳሰነች ወረዳ ከበኦሞ...

ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ 11ኛውን የኃይሌ ሆቴልና ሪዞርት በደብረ ብርሃን ከተማ አስመረቀ

ታዋቂው አትሌትና ባለሀብት ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ፣ በደብረ ብርሃን ከተማ...

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር የተዘጋጀው የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል ስቴት ኤግዘቢሽን ተከፈተ

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር አዘጋጅነት የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል...

በሊባኖስ እና በእሰራኤል የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት ተራዘመ

ትራምፕ በሊባኖስ እና በእሰራኤል መካከል የተደረሰው የተኩስ አቁም በሦስት...