የኢትዮጲያ ንግድ ባንክን አርማ (ሎጎ) ዲዛይን ያደረገው ማን እንደሆነ ያውቃሉ?

Date:

አቶ ናሥር ሐሰን ይባላሉ። አቶ ናሥር በቀድሞ ጊዜ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ም/ፕሬዝዳንት ነበሩ።

አቶ ናሥር ሐሰን በአሁኑ ጊዜ ነዋሪነታቸው በአሜሪካ ነው። አቶ ናስር የባንኩ አርማ ሲሰራ የነበረውን ሂደት በተመለከተ ያላቸውን ትዝታ እንዲህ በማለት ተናግረዋል፤

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን አርማ (ሎጎ) ሙያዬና ሥራዬ ባይሆንም ማንም ሳይጠይቀኝና ሳያዘኝ በራሴ ተነሣሽነት አንዲት ሣንቲም ሳይከፈለኝ ዲዛይን አድርጌና ክሊሼውን እንግሊዝ ሀገር በነፃ አሰርቼ ለወቅቱ የባንኩ ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ ለአቶ አለሙ አበራ አቅርቤ ሥራ ላይ እንዲውል ተደርጎ ላለፋት 50 ዓመታት አገልግሏል።

በመሆኑም አርማው በቼኮች በቁጠባ ሒሣብ ደብተሮችና በበንኩ የፅህፈት መሣሪያዎች ላይ እንዲታተም አስደረግኩ።

በወቅቱ የባንኩ የሒሣብና የኢንቬስትሜንት (መዋዕለ ንዋይ) መምሪያ ሥራ አስኪያጅ ነበርኩ።

በወቅቱ ለዚህ ሥራዬ የቃል ምስጋና እንኳን አላገኘሁም ነበር። አሁን ያን ወርቃማና ሽክርክር አርማ ለመተካት ግማሽ ቢሊዮን ብር ከማስወጣቱም በላይ በየሕንፃዎቹ ላይ ያሉትን አርማዎች አፍርሶ አዲሱን መተካት፣ ያሉትን የጽህፈት መሣሪያዎች የቼክና የቁጠባ ደብተሮች፣ የኮምፒዩተር ሶፍትዌሮችና ወዘተ ለመቀየር የሚወጣው ወጪ የትየሌሌ ነው።

በዚያ ላይ አዲሱን አርማ በመላ ዓለም ላሉ ባንኮች የፋይናንስ ድርጅቶች ለባንኩ ደምበኞች ሀ ብሎ ለማስተዋወቅ ሚሊዮኖች ያስወጣልና ትርፍና ኪሣራው በሚገባ ታስቦበታል ወይ ያሰኛል በማለት ይገልጻሉ አቶ ናሥር ሐሰን የቀድሞው የባንኩ ም/ፕሬዚዳንት

አቶ ናሥር ሐሰን በትጋት በታማኝነት፣ በቅንነት ከነበረባቸው ሃላፊነት በተጨማሪ ያሳዩት ትጋት የሚያስደንቅ እና የሚያስተምር ነው ።

ምንጭ፦ አብዱረሂም አህመድ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...