በመቀሌ የሰዎች አፈናና ድንገተኛ መሰወር ነዋሪዎችን አስደንግጧል

Date:



በትግራይ ክልል መቐለ ከተማ የሰዎች አፈና፣ ለገንዘብ ተብሎ የሚፈጸሙ እገታዎች፣ ዝርፊያ እና ምክንያቱ ያልታወቀ የሰዎች ደብዛ የመጥፋት እና መሰወር ሁኔታዎች በፍርሃት ውስጥ እንዲገቡ እንዳደረጋቸው ነዋሪዎች ገለጹ።


በቅርቡ አቶ ፊልሞን ገብረህይወት የተባለ የካሜራ ባለሙያ እና የፊላሪ ፕሮዳክሽን ባለቤት ከጠፋ ከሳምንት በላይ የሆናቸው ሲሆን እስከአሁን የት እንደደረሱ አልታወቀም።


የአቶ ፊልሞን ባለቤት ወይዘሮ ገነት እዝራ እንደተናገሩት ለመጨረሻ ጊዜ የባለቤታቸውን ድምጽ የሰሙት እሑድ ነሐሴ 11 ቀን 2017 ዓ.ም ምሽት ላይ በባጃጅ ወደ ቤቱ እየገባ በነበረበት ሰዓት ነው። “ወደ ቤት እየመጣሁ ነው አለኝ። እንደገና ደወልኩለት ነገር ግን አላነሳም በኋላ ላይ ስልኩ ጠፋ” ሲሉ ስለ ሁኔታው አስረድተዋል።


ወ/ሮ ገነት በማግስቱ ጠዋት ጉዳዩን ለፖሊስ ቢያሳውቁም ምንም አይነት መረጃ እንዳላገኙ ይናገራሉ። አለመረጋጋት በቤተሰቡ ላይ በተለይም በሁለት ትንንሽ ልጆቻቸው ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ መሆኑን አክለዋል። “ከአባታቸው ጋር ይህን ያህል ጊዜ ድረስ ተለያይተው አያውቁም። ለነሱ ሁሉ ነገራቸው ነው። አሁንም ዕለት ዕለት እየጠበቁት ነው። በጣም አስቸጋሪ ነው” ብለዋል።


መሰል ክስተቶች በመቐለ ከተማ ከቅርብ ወራት ወዲህ እየተባባሱ ስለመምጣታቸው ነዋሪዎች ይገልጻሉ። የ30 አመቱ ግርማይ ሃፍቴ “ከጦርነቱ በኋላ በፕሪቶሪያ ስምምነት መሰረት ትግራይን ለማስተዳደር ኃላፊነት የተጣለባቸው ሃይሎች ሰላም እና ጸጥታን ከማረጋገጥ ይልቅ በውስጥ የስልጣን ሽኩቻ ውስጥ ገብተዋል” በማለት ሁኔታውን “ፍፁም ውድቀት” ሲሉ ገልጸውታል።  አስ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...