የገንዘብ ሚኒስቴር በአዲሱ የገቢ ግብር አዋጅ ላይ የሰጠዉ ማብራሪያ

Date:



  1. በገቢ ግብር (ማሻሻያ) አዋጅ ቁጥር 1395/2017 አንቀጽ 89 እንደተመለከተው ግብር ከፋዮች በየሶስት ወሩ ለሚከፍሉት ግብር መሰረት የሚሆነው ከተያዘው የግብር ዓመት በፊት በነበረው የግብር ዓመት የከፈሉት ግብር ነው::
  2. ከተያዘው የግብር ዓመት በፊት በነበረው የግብር ዓመት የከፈሉት ግብር ማለት ደግሞ ባለፈው አመት ከተከፋይ ሂሳብ ላይ ተቀንሶ የተከፈለውን እና ወደአገር በሚያስገቡት እቃ ላይ የተከፈለውን ግብር እንዲሁም እነዚህ ሂሳቦች ተቀንሰው በአመቱ መጨረሻ አስታውቀው የከፈሉትን ግብር ይጨምራል፡፡
  3. በመሆኑም ከተከፋይ ሂሳብ ላይ ተቀንሶ የተከፈለው እና ወደአገር በሚያስገቡት እቃ ላይ የክፈሉት ግብር በየሶስት ወሩ ለሚከፈለው 25% ግብር ስሌት መሰረት መሆን አለበት፡፡

ከተከፋይ ሂሳብ ላይ ተቀንሶ የተከፈለው እና ወደአገር በሚያስገቡት እቃ ላይ የተከፈለው ግብር በየሦስት ወሩ 25% ለሚከፈለው ግብር ክፍያ ተቀናሽ የሚደረገው የወቅቱ የግብርዘመን ሲሆን በየካቲት ወር 2018 ለሚፈፅሙት የመጀመሪያው 25% ግብር ክፍያ ተቀናሽ የሚደረገው ቅድመ ግብር የሐምሌ 2017፣ የነሐሴ 2017 እና የመስከረም 2018 ዓ.ም (ከሂሳብ ጊዜያቸው የመጀመሪያዎቹ ሶስት ወራት) ነው፡፡ የሁለተኛ እና የሶስተኛ 25% ክፍያም ላይተቀናሽ የሚደረገው እንደቅደም ተከተላቸው የየሶስት ወራቱ ይሆናል፡፡

እ.ኤ.አ December 31 ሂሳባቸውን የሚዘጉ ግብር ከፋዮች የ2025 የመጀመሪያው 25% ግብር ክፍያ የሚፈፅሙት August 2025 ሲሆን ተቀናሽ የሚደረገው ቅድመ ግብርየJanuary, February እና March 2025 (ክሂሳብ ጊዜያቸው የመጀመሪያዎቹ ሶስት ወራት) ነው፡፡ የሁለተኛ እና የሶስተኛ 25% ክፍያም ላይ ተቀናሽ የሚደረገው እንደቅደም ተከተላቸው የየሶስት ወራቱ ይሆናል፡፡

በዚህ ተራ ቁጥር ከተሰጠው ማብራሪያ ጋር ተያይዞ ግብር ከፋዮች የሚያነሱት ተጨማሪ ጥያቄ ወይም ድጋፍ ካለ በታክስ አስተዳደር አዋጁ በተደነገገው አግባብ በመ/ቤታችሁ ምላሽ ይሰጣቸው፡፡

  1. ሂሳባቸውን እ.ኤ.አ. በዲሴምበር 2024 የሚዘጉ ግብር ከፋዮች ያቀረቡት የገቢ ማስታወቂያ ኪሳራ ወይም ምንም አልሰራንም የሚል ከሆነ በየሶስት ወሩ የሚከፈለው ግብር የሚሰላው እ.ኤ.አ. ከ2024 በፊት ካሉት የግብር አመታት ውስጥ በመጨረሻ ግብር በተከፈለበት አመት የከፈሉትን ግብር መሰረት በማድረግ ይሆናል፡፡
  2. ሆኖም ግብር ከፋዮች ፀንተው ስራ ላይ ባሉ የታክስና ሌሎች ሕጎች ሰነዶችን ይዞ ስለማቆየት በተደነገጉት አንቀፆች ከተጠቀሱት አመታት በላይ ያለውን የግብር አመት አይጨምርም፡፡ ከዚህ ውጪ ባለፉት አመታት ምንም አይነት ግብር ያልከፈሉ ከሆነ በተያዘው የግብር አመት ሶስት ወራት ባከናወኑት የንግድ ስራ እንቅስቃሴ ላይ ሊከፍሉት የሚገባው ግብር ተሰልቶ ሊከፍሉ ይገባል፡፡
  3. በገቢ ግብር አዋጁ በተፈቀደው መሰረት ያጋጠማቸው ኪሳራ በመሸጋገር ላይ ያለ ግብር ከፋዮች አማራጭ አነስተኛውን ግብር 2.5% ከፍለው ከዚያ በላይ ሊከፍሉት የሚገባ ግብር ካለ ኪሳራው ከ2.5% በላይ ከሆነው ግብር ጋር ይካካሳል፤ በዚህ አይነት ሊካካስ የሚችል ግብር ከሌለ ኪሳራው ወደሚቀጥለው የግብር አመት ይሸጋገራል፡፡
  4. አማራጭ አነስተኛ ግብር (2.5%) የሚከፍሉ ግብር ከፋዮች ሊከፍሉት የሚገባው ግብር ሲሰላ በግብር አመቱ ከተከፋይ ሂሳብ ላይ ተቀንሶ የተከፈለው ግብር እና ወደአገር በሚያስገቡት እቃ ላይ የከፈሉት ግብር ተቀናሽ ይደረጋል፡፡
  5. በገቢ ግብር አዋጅ ማሻሻያ አንቀጽ 23 በተመለከተው መሰረት አማራጭ አነስተኛ ግብር ለ5 አመታት የሚሸጋገር መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ፤ አማራጭ አነስተኛ ግብር ስራ ላይ ከዋለበት ጊዜ ጀምሮ ኪሳራ ወይም ምንም አልሰራንም የሚል ማስታወቂያ የሚያቀርቡ ግብር ከፋዮች አነስተኛውን ግብር የሚከፍሉ ስለሆነ፤ በሚቀጥለው የግብር አመት በየሶስት ወሩ ለሚከፍሉት ግብር መሰረት የሚሆነው የከፈሉት አማራጭ አነስተኛ ግብር ነዉ።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...