መልካም የአፍ ጠረን አስፈላጊና በአጋጣሚ ሰዎችን ሲቀርቡ እንዳይሳቀቁ ያደርጋል።
የአፍ ንጽህና ጉድለት መንስኤዎች
በጥርስና አፍ ውስጥ የሚቀሩ የምግብ ቅሪቶች፣ ከተመገቡ በኋላ አፍ አለመጉመጥመጥ፣ ጥርስን አለመቦረሽና አፍን አለመታጠብ፣ ሲጋራ አልኮል መጠጥና መሰል ሱስ፣ በቂ ውሃ አለመጠጣት፣ ሽንኩርትና ቅመም የበዛባቸው ምግቦች፣ ስኳር የበዛባቸውን ምግቦች ማብዛት።
አንዳንድ መድሃኒቶች ለአፍ ጠረን መቀየር ምክንያት ይሆናሉ፤ የአፍ ውስጥ፣ የድድ እና የጥርስ ህመምና ተያያዥ ችግሮች፣ የአፍ ውስጥ ቁስለትና ባክቴሪያ እንዲሁም እንደ ካንሰርና ስር የሰደደ የጨጓራ ቁስለት ህመም።
የአፍ ጤንነትን ለመጠበቅ
በቀን ሁለት ጊዜ ጥርስ እና ምላስን ማፅዳት
ፍሎስ ማድረግ (በጥርስ መሃል ያሉ የምግብ ቅሪቶችን ማስወገድ)
በብዛት ውሃ መጠጣት
ከስኳር ነፃ የሆነ ማስቲካ ወይም ሚንት መጠቀም፦ ተፈጥሯዊ የአፍ ማጽጃ የሆነውን ምራቅ ለማምረት ይረዳል።
መጥፎ የአፍ ጠረን የሚያስከትሉ ባክቴሪያዎችን የሚዋጉ ፕሮባዮቲክስ ስለሚይዙ እንደ እርጎ እና አይብ ያሉ የወተት ተዋጽኦዎችን መጠቀም።
ከዕፅዋት የተዘጋጁ ሻዮች፦ ተፈጥሯዊ ትንፋሽ የማደስ ባህሪ ካላቸው ዕፅዋት የተቀመመ ሻይ እንደ ፔፐርሚንት ወይም ኮሞሜላን መጠጣት።
እንደ ሴሊሪ እና ካሮት ያሉ ጥሬ አትክልቶችን መመገብ ጥርስዎን ለማጽዳት እና ትንፋሽን ለማደስ ይረዳሉ።
የጥርስ ቡርሽዎን ቢበዛ ከሦስት ወር በላይ አለመጠቀምና በንጽህና መጠቀም።
በተቻለ መጠን በየጊዜው መደበኛ የአፍና የጥርስ ምርመራዎችን ማድረግ ይልመዱ።
