በ6ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርኃ ግብር ማንችስተር ዩናይትድ ከሜደው ውጭ ከብሬንትፎርድ ጋር ያደረገው ጨዋታ በባለሜዳዎቹ 3 ለ 1 አሸናፊነት ተጠናቅቋል፡፡
ጨዋታው በተጀመረ በ20 ደቂቃ ውስጥ ኢጎር ቲያጎ የብሬንትፎርድን ሁለት ግቦች ያስቆጠረ ተጫዋች ሲሆን ሶስተኛ ግቧን ደግሞ ማቲያስ ጄንሰን ከመረብ አሳርፏል፡፡
ማንችስተር ዩናይትድን ከሽንፈት ያልታደገች ብቸኛ ግብ ቤንጃሚን ሼሽኮ ከእረፍት በፊት አስቆጥሯል፡፡
በጨዋታው ለማንችስተር ዩናይትድ የተሰጠውን የፍጹም ቅጣት ምት አምበሉ ቡርኖ ፈርናንዴዝ ሳይጠቀምበት ቀርቷል፡፡
ፕሪሚየር ሊጉ ከተጀመረ 6 ሳምንታት የሆኑት ሲሆን፤ ማንችስተር ዩናይትድም ከወዲሁ 3ኛ ሽንፈቱን አስተናግዷል፡፡
