የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሁለት ግዙፍ የሩሲያ የነዳጅ ዘይት ኩባንያዎች ላይ ማዕቀብ ለመጣል ማቀዳቸውን አስታውቀዋል።
ይህም ሞስኮ ከዩክሬን ጋር በቀረበው የሰላም ዕቅድ እንድትስማማና ወደ ድርድር እንድትመጣ ጫና ይፈጥርባታል ተብሏል።
ዶናልድ ትራምፕ አክለውም “ከፑቲን ጋር ሁልጊዜም ጥሩ ውይይቶችን እናደርጋለን ነገርግን ፈፅሞ የትም ተራምደው አያውቁም ተግባራዊነት የላቸውም ሲሉ”!ከኔቶ ዋና ፀሀፊ ማርክ ሩቴ ጋር በነበራቸው ውይይት ኋላ አስታውቀዋል።
በዋሺንግተንና በአውሮፓ ህብረት መሪዎች የቀረበውን የሰላም ስምምነት ዕቅድ ፑቲን እንዲቀበሉ በማዕቀብ ጫና ማሳደር አስፈላጊ መሆኑን ትራምፕ ገልፀዋል።
“ፑቲን ወደ ውይይት ይመጣል፤ ማዕቀብ ከጣልን የትም አይሄድም!” ብለዋል ትራምፕ
ትራምፕ ማዕቀብ ሊጥሉባቸው ያቀዷቸው ግዙፍ የሩሲያ የነዳጅ ዘይት ኩባንያዎች ሮዝኔፍትና ሉክኦይል ይሰኛሉ።
ዶናልድ ትራምፕ የማዕቀብ መጣሉን ሀሳብ ያቀረቡት ከፑቲን ጋር በቡዳፔስት ሊያካሂዱ የነበረው ስብሰባ ላልተወሰነ ጊዜ መራዘመን በገለፁበት ማግስት ነው።
ሞስኮ በዩክሬን መዲና ኬቭና ሌሎች ከተሞች ላይ የሚሳኤልና የድሮን ናዳ ማዝነቧን ቀጥላለች።
በትላንትናው እለት በፈፀመችው ጥቃት ሰባት ሰዎች ህይወት ማለፉንና በርካቶች መቁሰላቸው ይታወሳል።
NBC Ethiopia
